Connect with us

በሀሰተኛ መታወቂያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

ፖሊስ ነኝ በሚል ሀሰተኛ መታወቂያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ
Photo: Social Media

ዜና

በሀሰተኛ መታወቂያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ስሙ ሳህሊተምህረት ቤተክርሲቲያን አካባቢ ፖሊስ ነኝ በሚል ሀሰተኛ የመከላከያ መታወቂያ በማሳየት ከባድ የውንብድና ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በተመሰረተበት ክስ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡

ተከሳሽ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 671(1) (ለ) በመተላለፍ ከቀኑ 8 ሰዓት ሳህሊተምህረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አይናለም እና ሄኖክ የሚባሉ የግል ተበዳዮችን ካልተያዙ ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን የሰሌዳ ቁጥር 3-53047 አ/አ የሆነ ሀይሉክስ ቶዮታ መኪና በተከሳሽ አሽከርካሪነት በተጠቀሰው ቦታ ሲደርሱ ፖሊሶች ነን ትፈለጋላችሁ በሚል የመከላከያ መታወቂያ በማሳየት የግል ተበዳዮችን አስገድደው አጃቸውን በማሰር በመኪናቸው ጭነው ካራ ተብሎ ወደ ሚጠራው አካባቢ በመውሰድ ከ1ኛ ተበዳይ 5000 የእንግሊዝ ፓውንድ በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር አንድ መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ብር እና የዋጋ ግምቱ አራት ሺ አምስት መቶ የሆነ ሂዋዌ ምባይል ከ2ኛ ተበዳይ አስራ ስምንት ሺ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ሞባይል የወሰዱ ሲሆን በአጠቃላይ ሁለት መቶ አስራ ሰባት ሺ አምስት መቶ ብር የሚገመት ንብረት አስገድደው ከተቀበሏቸው በኋላ መንገድ ላይ ገፍትረው ጥለዋቸው የሄዱ በመሆኑ የተያዘው ተከሳሽ በፈፀመው የከባድ ውንብድና ወንጀል ተከሷል፡፡

ዐቃቤ ሕግም የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን የክስ ዝርዝሩ በችሎት የተነበበለት ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለቱ የምስክሮች ቃል በችሎት ተሰምቷል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽን በተከሰሰበት ክስ ጥፋተኛ በማለት ነሀሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
(#ኢፕድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top