Connect with us

የስኳር ኘሮጀክቶችን እርቃናቸውን ያስቀረው- ሜቴክ!

የስኳር ኘሮጀክቶችን እርቃናቸውን ያስቀረው- ሜቴክ!
Photo: Social Media

ኢኮኖሚ

የስኳር ኘሮጀክቶችን እርቃናቸውን ያስቀረው- ሜቴክ!

የስኳር ኘሮጀክቶችን እርቃናቸውን ያስቀረው- ሜቴክ!
~ በዘርፉ ከ9 ቢልየን ብር በላይ ኪሳራ ተመዝግቧል

የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች «እየሰራን እንማራለን» በሚል ድፍረትና በቂ የገንዘብ አቅም በሌለበት መጀመራቸው ላለመሳካታቸው ምክንያት እንደሆነ የስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ።

ሥራ አስፈፃሚው አቶ ጋሻው አይችሉህም በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደተናገሩት፤ ፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅም ሆነ መሳካት ያልቻሉት ሲቋቋሙ በቂ የአዋጭነት ጥናት አለመጠናቱ፤ በቂ የገንዘብ አቅም በሌለበት ሁኔታ መጀመራቸው እና ለፋብሪካዎቹ የተመረጡት አካባቢዎች ቆላማ እና ምንም ዓይነት መሠረተ ልማት የሌለባቸው በመሆናቸው ነው።

በተጨማሪም የወሰን ማስከበር ችግር፤ ሥራውን የወሰደው ኮንትራክተርም በቂ ልምድ ሳይኖረው «እየሰራን እንማራለን» ብሎ በድፍረት ብቻ ያለ በቂ እውቀት ሥራውን መጀመሩ ለፕሮጀክቶቹ አለመሳካት ዋንኛ ተግዳሮቶች እንደነበር አመልክተዋል። በ2003 ዓ.ም በአገሪቱ ሊሰሩ የታቀዱትን አስር ፋብሪካዎች በ18 ወራት ለመጠናቀቅ ውል ፈርሞ የተቀበለው የኢትዮጵያ ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የችግሩ ዋንኛ ባለቤት መሆኑንም አስታውቀዋል።ሜቴክ ያለምንም በቂ ሥራ በርካታ ገንዘብ መውሰዱን ያመለከቱት ሥራ አስፈጻሚው፣ በወቅቱ የነበረው የስኳር ኮርፖሬሽኑ የማስፈፀም አቅምም አነስተኛ እንደነበር ገልጸዋል።

እንደ አቶ ጋሻው ገለፃ፤ ጥናት ተደርጎባቸው ኪሳራቸው የተለዩት የጣና በለስ ቁጥር 1 እና 2 የኦሞ ፣ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካዎች በውሉ መሠረት በተቀመጠላቸው የግንባታ ጊዜ ተጠናቀው ወደምርት ባለመግባታቸው ኪሳራ ደርሶባቸዋል። ለብክነቱም ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦች ጉዳይም በሕግ አግባብ እየታየ መሆኑን አመልክተዋል ።

ኮርፖሬሽኑ ከ2006 እስከ 2010ዓ.ም ድረስ ባጠናው ጥናት ከ9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን ገልፀዋል። ለኪሳራውም ምክንያት ከፋብሪካው ግንባታ በፊት የተተከለ ሸንኮራ አገዳ የማስወገድ ሥራ መሰራቱ፤ ሥራው ይጀመራል ተብሎ የተቀጠሩ ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ፤ የዓለም አቀፍ አማካሪዎች ክፍያና የባንክ ወለድና ገቢ ያልሆነ ገንዘብ በአጠቃላይ ተደምሮ መሆኑን አስረድተዋል።

ሜቴክ ከ10 ፋብሪካዎች፤ ማለትም በጣና በለስ ስር ሦስት ፋብሪካ ለመስራት ታቀዶ በፋይናንሰ ችግር ምክንያት ጣና በለስ ቁጥር 3 እንዲቀር መደረጉን አመልክተው፣ በኦሞ ኩራዝ ልማት ፕሮጀክት ላይ የኦሞ ኩራዝ ላይ 5 ፋብሪካዎች ታቅደው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር አራት ሳይጀመር መታጠፉን አስታውቀዋል።

ኮንትራቱን የወሰደው ሜቴክ ጭራሽ ያልጀመራቸው ፋብሪካዎች እንደነበሩ አመልክተው፣ በዚህ የተነሳ የወልቃይት ልማት ፕሮጀክትና የከሰም ልማት ፕሮጀክትን ከእጁ በማውጣት ለቻይና ኩባንያዎች መሰጠታቸውን ጠቁመዋል።

ሜቴክ አፈፃፀሙ ዝቅተኛ ቢሆንም ከስር ከስር ገንዘብ ይከፈልው የነበረ ሲሆን ኮርፖሬሽኑም አቅም ሳይኖረው ከአፈፃፀም በታች መሆኑን እያወቀ ከፍተኛ ክፍያ ይከፍል እንደነበር አመልክተዋል።
(አዲስ ዘመን ነሃሴ 18/2012)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top