Connect with us

ብሄራዊ ባንክ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ ውጭ ማከማቸትን ከለከለ

ብሄራዊ ባንክ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ ውጭ በቤትም ሆነ በሌላ ቦታ ማከማቸትን ከለከለ።

ኢኮኖሚ

ብሄራዊ ባንክ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ ውጭ ማከማቸትን ከለከለ

የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድረስ በቤትም ሆነ በሌላ ቦታ መያዝ እንደሚፈቀድና ከዚህ በላይ ገንዘብ ይዞ መገኘት እንደሚያስቀጣ ይፋ አድርገዋል።

የባንኩ ገዥ ይህን ያሉት ብሄራዊ ባንክ ያወጣቸውን አራት መመሪያዎችን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫን በሰጡበት ወቅት ነው።

ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን በላይ ከባንክ ውጪ ማስቀመጥ መከልከሉም ሀገሪቱ የምታሳትመው የገንዘብ ኖት በተገቢው መልኩ ኢኮኖሚው ውስጥ እንዲዘዋወር ያግዛል ማለታቸውን ፋብኮ ዘግቧል። ህገ ወጥነትን ለመከላከል እንደሚያግዝም ገልጸዋል።

የገንዘብ ኖት ባልተገባ ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋሉ ሀገሪቱ በውጭ ምንዛሬ የምታሳትመው የገንዘብ ኖት እየተበላሸ ለተጨማሪ ወጪ እንደዳረጋትም ዶክተር ይናገር አንስተዋል።

ማንኛውም ሰው ገንዘብ እንዳይጎዳ አድርጎ እንዲይዝና የትኛውም አካል ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ከባንክ ውጪ እንዳያስቀምጥ፣ ማንኛውም ድርጅት ኤ ቲ ኤም እና መሰል የዲጂታል የግብይት ስርአትን እንዲጠቀም፣ ባንኮች ከውጪ መበደር እንዲችሉ የሚል እና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወደ ባንክ እንዲያድጉ መፈቀዱን የሚገልጹ መመሪያዎችን ነው ብሄራዊ ባንክ ያወጣው።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top