Connect with us

ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ሙላቱ ለማ የአሜሪካን ፕሬዚደንታዊ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ሙላቱ ለማ የአሜሪካን ፕሬዚደንታዊ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
Facebook Never be afraid. Dr. Mulatu Lemma... - Savannah State University

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ሙላቱ ለማ የአሜሪካን ፕሬዚደንታዊ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

በአሜሪካ የሳቫና ስቴት ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ፕሮፌሰር የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ሙላቱ ለማ የአሜሪካን ፕሬዚዳንታዊ የሳይንስ፣ የሒሳብ እና የምሕንድስና የልህቀት ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

ዶ/ር ሙላቱ ትምህርታቸውን ኢትዮጵያ እንደጀመሩ እና የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን በአፕላይድ ማቲማትክስ ሀገራቸው ውስጥ እንዳገኙ ተገልጿል።

ወደ አሜሪካ ካቀኑ በኋላም እ.አ.አ በ1993 በፒዩር ማቲማቲክስ ማስተርስ እንዲሁም በ1994 በዚሁ ትምህርት ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) አግኝተዋል።

ዶ/ር ሙላቱ እ.አ.አ በ2011 በስማቸው የተሰየመ “የሙላቱ ቁጥር” የተሰኘ የሒሳብ ቀመር ለዓለም አስተዋውቀዋል።
በሳቫና ስቴት ዩኒቨርሲቲ በሒሳብ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እየሠሩ የሚገኙት ዶ/ር ሙላቱ፣ ከ100 በላይ የምርምር ጥናቶችን ማዘጋጀታቸውም ነው የተነገረላቸው።

በሥራቸውም በተለያዩ ጊዜያት በርከት ያሉ ሽልማቶችን ማግኘታቸው ተጠቁሟል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለዶ/ር ሙላቱ ለማ የእንኳን ደስ ያለዎ መልእክት አስተላልፏል። #EBC

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top