Connect with us

እንዴት ነው ነገሩ?

እንዴት ነው ነገሩ?
Photo: Social Media

ትንታኔ

እንዴት ነው ነገሩ?

እንዴት ነው ነገሩ?
(ሙሼ ሰሙ)

ሕገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር፤ ጥያቄያችን ጆሮ ይሰጠው በማለት መሳርያ ሳይታጠቁ፣ ገጀራ፣ ሜንጫና ጦር ሳይሰብቁ፣ የማንንም ንብረት ሳያወድሙና ሰው ሳይገድሉ፣ ልዩ ሃይለ አደባባይ ሳያወጡ፣ አቤት በሚሉ የወላይታ ሕዝቦች ላይ ሰራዊት ማዝመት ለምን አስፈለገ? ለሕዝብ ጥያቄ ፣ መልሱን የማውቅልህ እኔ ነኝ ማለት ፋሽኑ ዛሬም አላለፈበትም ማለት ነው?!

የዜጎቹን የመብት ጥያቄ “ከዚህ በላይ አልታገስም” በማለት በሀይል መቀልበስ እንደማያዛልቅ ከቀደምት ገዢዎች ተሞክሮ በመውሰድ ወደ ክብ ጠረጴዛ ተመልሶ ጥያቄውን በድርድር በመፍታት፣ ክቡር የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ፣ ጊዜና ሀብት እንዳይባክን ማድረግ ብልህነት ነው ።

የደቡብ ክልል ሕዝብ ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ በሕዝብ ፍላጎትና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዘለቄታ ያለው መፍትሔ መስጠት በየጊዜው ከሚያገረሽ የግጭት አዙሪት እንደ ሀገርም ሆነ ሕዝብ ሁላችንንም ይታደገናል።

ለ27 ዓመት ጥያቄያቸው ተገፍቷል፣ በውጣ ውረድም ከድህነት የመላቀቂያ ጊዜያቸው ባክኗል፣ አሁንም ኢትዮጵያዊ ናችሁ ማለት ብቻ አይበቃም። ጥያቄያቸው ፈጣን ምላሽ አግኝቶ ወደ ስራ ይግቡ። እንደሌላው ሕዝብ ከመብት ጥየቃ ተላቀው ትኩረታቸውን ወደ ድህነት ቅነሳና ልማት ያድርጉ።

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top