Connect with us

“በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብፅና ሱዳን የሚፈልጉት አሳሪ ስምምነት ፈፅሞ አይሰራም” – ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ

“በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብፅና ሱዳን የሚፈልጉት አሳሪ ስምምነት ፈፅሞ አይሰራም” - ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ
Photo: EPA

ትንታኔ

“በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብፅና ሱዳን የሚፈልጉት አሳሪ ስምምነት ፈፅሞ አይሰራም” – ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ግብፅና ሱዳን የሚፈልጉት አሳሪ ስምምነት የማይሰራና መርህን ያልተከተለ ነው ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ ገለጹ። ኢትዮጵያ የያዘችው አቋም ትክክለኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፖለቲክስና የአፍሪካ ጥናት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በህዳሴው ግድብ ላይ የሚያራምዱት አቋም ለድርድሮቹ ውጤታማነት እንቅፋት ሆኗል፡፡
በውሀው ሙሌትና በአየር ለውጥ በተለይም በድርቅ ጊዜ ኢትዮጵያ ከግድቡ እንድትለቅ የሚጠይቁት የውሀ መጠን መርህን ያልተከተለና የማይሰራ ነው።

የታችኛው ተፋሰስ ሀገራቱ የሚፈልጉት አሳሪ ስምምነት ለአሁን ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ትውልዱ እንዲተገብረው የሚያስገድድና ወቅታዊ ሁኔታን የማያገናዝብ መሆኑን ጠቁመዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተከትሎ የሚመጣ ድርቅ መተንበይ ከባድ መሆኑን ገልፀው፤ አለምን ስጋት ላይ በጣለ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ መሰረት አድርጎ አሳሪ ስምምነት ላይ መግባባት እራስን እንደመርሳት ነው ብለዋል።

ግብፅና ሱዳን የሚፈልጉትን ‹‹በድርቅ ጊዜ ካጠራቀማችሁት ውሀ ትሰጡናለችሁ›› የሚለውን አሳሪ ስምምነት ኢትዮጵያ አለመቀበሏን ገልፀው፤ ይህም አቋም ትክክል መሆኑን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያቀረቡት አሳሪ ስምምነት ውስጥ ፈፅሞ መግባት የለባትም ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ሀገሪቱ አሁን በያዘችው አቋም መፅናት አንዳለባት አሳስበዋል።

ሀገራቱ በቀላሉ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው የገለፁት የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ፣ ለዚህም ደግሞ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚያቀርቡት አሳሪ ስምምነት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

በግድቡ ዙሪያ በየጊዜው በተለዋዋጭ ሁኔታ ተለዋዋጭ ውሳኔ የሚሰጥበት አካሄድ መተግበር ይገባዋል የሚሉት ፕሮፌሰር ተስፋዬ፣ አሁን ላይ ወደፊት በሚመጣ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰት የውሀ ይለቀቅልን ስምምነት ግን ተገቢነት የሌለውና መርህን ያልተከተለ መሆኑን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ያላት አቋም ትክክል በመሆኑ ልትፀና ይገባል ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ መንግስት በተለይ ከአሜሪካ መልስ የኢትዮጵያን ጥቅም የማስጠበቅ አቋም ማራመዱ የሚደነቅ መሆኑንም ገልፀዋል። ግድቡ በተመለከተ የተለያየ የውጪ ሀይሎች በመንግስት ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ገልፀው እነዚህን ጫናዎች ተቋቁሞ የሀገሪቱን ጥቅም ለማስጠበቅ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

በተለያዩ ጫናዎች ውስጥ ሆኖ የኢትዮጵያ መንግስት በግድቡ ላይ የሀገሪቱን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገው ጥረት ከህዝቡ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚገባና ወደፊት በድርድር ሂደት የሚካሄዱ ስምምቶች የሀገርን ጥቅም ያስጠበቁ እንዲሆኑ በጋራ መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top