Connect with us

ማሰብ ከተሳነው ጋር ክርክር

ማሰብ ከተሳነው ጋር ክርክር
Photo: Social Media

ትንታኔ

ማሰብ ከተሳነው ጋር ክርክር

ማሰብ ከተሳነው ጋር ክርክር

(ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

ነሐሴ 2012

አንድ የመንግሥት ካድሬ ከኢሳት ቲቪ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደተረዳሁት ከሀጫሎ መገደል በኋላ በኦሮምያ የተፈጸመው ግድያ፣ ቃጠሎና ግርግር ከጎሣም ሆነ ከሃይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት አልነበረውም ብሎ አጠንክሮ ተከራከረ፤ የካድሬው ክርክር እኔን ግራ አጋብቶኛል፤ አስተያየቶችን እናቆይና ወደእውነቱ እንግባ፤– የማይካዱትን ሁነቶች እንያቸው፡–

1. በጊዜው፣ ግድያው፣ ቃጠሎውና ግርግሩ የተፈጸመበት ክልል ኦሮምያ ነው፤

2. የተገደሉት ከተለያዩ ጎሣዎች ቢሆኑም አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው፤

3. የተገደሉት ሁሉ ክርስቲያኖች ናቸው፤

4. የተገደሉት ኦሮሞዎች ሁሉ ክርስቲያኖች ናቸው፤

5. ማስረጃ ባይኖርም ገዳዮች አማራዎች አልነበሩም፤

6. ማስረጃ ባይኖርም ገዳዮች ኦሮሞዎች ነበሩ፤

7. እስላሞች አልተገደሉም፤

እነዚህን እውነቶች መቀበል ብዙ የመመርመርን፣ የመሥራትንና አስፈላጊውንም ለውጥ ለማድረግ ከባድ ኃላፊነትን በአገዛዙ ላይ ይጭኛል፤ ይህ ግዴታ ነው፤ ምርጫ አይደለም፤ ዓይንን ሸፍኖ ሕዝቡ ምንም አላየም ማለት እንደኔ አትዩ እያሉ ማዘዝ ነው፤ ሁላችንም እያየን የምናየው የተለያየ ቢሆንም ብንመረምረውና ብንወያይበት አቧረው ሲገፈፍ ሁላችንም እኩል ማየት እንችል ይሆናል፡፡

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top