Connect with us

” 125 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ” ኢንጂነር ታከለ ኡማ

" 125 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ" ኢንጂነር ታከለ ኡማ
Photo: Facebook

ዜና

” 125 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ” ኢንጂነር ታከለ ኡማ

በአዲስ አበባ ከተማ በተመጣጣኝ ዋጋ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማቅረብ 125 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በግንባታ ላይ እንደሚገኙ ኢንጅነር ታለከ ኡማ ገለፁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን በዚህ ወቅት ምክትል ከንቲባው የ2012 በጀት አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።

በዚህ ሂደት ላይ ውዝፍ የባንክ ቤት እና የወሰን ማካላል ሂደቶች ችግር ቢፈጥሩም ምክትል ከንቲባው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዜጎች ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በግንባታ ላይ ከሚገኙ የጋራ መኖርያ ቤቶች መካከል 95 ሺህ የሚሆኑት የ20/80 ቤቶች መሆናቸውን ያስታወቁት ኢንጅነር ታከለ ኡማ 29 ሺህ ቤቶች ደግሞ በ40/60 መርሃግብር በግንባታ ላይ ናቸው ብለዋል።

ምክትል ከንቲባው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፓርት ባለፉት ሁለት ዓመታት የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።

በተለይ ለበርካታ ዓመታት በከተማው አስተዳደር ትኩረት ሳይሰጣቸው የቆዩ አርሶ አደሮችን በተለያዩ ዘርፎች የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።

በተመሳሳይ በከተማዋ የሸገር ዳቦ ፣ እንስራ የገበያ ማዕከል ፣ ፣ የሸማ ማዕከላት፣ የትምህርት ቤቶች እድሳት እና የእጦጦ መነፈሻን የመሰሉ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ምክል ከንቲባው ተናግረዋል።

ለዚህም የፌዴራል መንግስት ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበረ አንስተዋል።

ከተማዋ ሁሉንም በእኩልነት የምታስተናግድ ፣ አቅመ ደካሞችን የማትዘነጋ፣ እና ተስፈኛ ተማሪዎችን ለመፍጠር የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸው ተጠቁሟል።

#FBC

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top