Connect with us

“አብይ አሕመድ ወንድ ነው‼” – የግብጻዊዩ ሙዕተዝ አስገራሚ ትንታኔዎች

አብይ አሕመድ ወንድ ነው‼ - የግብጻዊዩ ሙዕተዝ አስገራሚ ትንታኔዎች
Photo: Social Media

ትንታኔ

“አብይ አሕመድ ወንድ ነው‼” – የግብጻዊዩ ሙዕተዝ አስገራሚ ትንታኔዎች

🌿አብይ አሕመድ ወንድ ነው‼ – የግብጻዊዩ ሙዕተዝ አስገራሚ ትንታኔዎች

«.. መቸም ይሄንን አንብቦ የማይገረም የለም..»
ሙዕተዝ ይባላል። የአረቡ አካባቢ ታዋቂና ዝነኛ አክቲቪስት እና የፖለቲካ ተንታኝ ነው። ዜግነቱ ግባፃዊ ነው። የመጨረሻ ዛሬ ሀቁን ተናገረ። በመጀመሪያም አለ የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ። አዎ እንኳን ደስ አላችሁ አለ። ደጋግሞ የእንኳን ደስ አላችሁ መልክቱን ተናግሮ። አብይ አሕመድ ወንድ ነው አለ። እናቱ የወለደችው ለኢትዮጵያ ሞቶ ጥቅሟን ያዳነ ጀግና ነው።

አብይ ከልጅነቱ እስከ መንግስት ስልጣነ ብትር መቆጣጠር ድረስ የሀገሩን ችግር የሚያውቀውና በጦር ሜዳ ተፈትኖ ያደገ ሰው ነው አለ። የእኛ መንግስት ከአብይ አሕመድ ጋር ይወዳደር ከተባለ አልሲሲ (የሃገሩን ፕሬዚዳንት ማለቱ ነው)፣ ቂጣ እየጋገረ ከአንድ ትምህርት ቤት ወደ ሌላ ትምህርት ቤት በመውሰድ ያደረገ ሰው ነው አለ። የፖለቲካ እውቀቱም ነገር ማመላለስ ነው አለ። ነገር እያመላለሰ ሊቢያን አፈረሰ፣ በነገር ማመላለስ በሽታ ተሞ አላቅሙ ቱርክን እዋጋለሁ ብሎ ፎከረ፤ ያንንም ፈረቶ ሳይዋጋ ቀረ። ተዋርዶ መሳቂያ ሆነ አለ።

አስታውሳለሁ አለ። አንድ ቀን አብይ አሕመድ በፓርላማ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በአባይ ግድብ ዙሪያ አይደራደርም እኛም መሪዎቿ ጥቅሟን አሳልፈን ሰተን የነገ ታሪካችንን አናበላሽም ብሎ ለህዝቡ ሲናገር።

የእኛ መንግስት የአብይን ንግግር ሰምቶ የፓርላማውን በአስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ አሜሪካ ከጎናችን ናት፤ ትራንፕ አለን ብሎ ተናገረ። መጨረሻ ላይ ግን በየሃገሩ ህዝቦች ኮርቶ መሃላ የፈፀመው አብይ አሕመድ አሸነፈ አለ።

ጋዜጠኛው አብይ እንዴት አሸነፈ ብሎ ጠየቀው?
የሙዕተዝ መልስ [.አሜሪካ በግድ ፈርም ስትለው አልፈርምም የአንችንን አደራዳሪነት አልሻም አላት። የአውሮፓ ህብረት ላደራድርህ አለው.? አይ ጉዳዩ ወደ አፍሪካ ህብረት ይመለስ ብሎ ሸውዷቸው ከአውሮፓ ወደ አፍሪካ መለሰው አለ። አልሲሲና ዶናልድ ትራንፕ አብይን ደውለው ውሀ እንዳትሞላ ብለው ለማስፈራራት ሞከሩት፦ ከምንም ሳይቆጥራቸው ሞልቶ ከጨረሰ ቡሀላ ሞልቼ ጨረስኩ ብሎ ለሃገሩ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ሲያስተላልፍ ሰሙት አለ።

አይሁዱን ትራፕ ያመነው የኛ ፊራኡን ( ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ሲሲ ማለቱ ነው ) ምንም ነገር ሳያገኘ ተሸነፈ አለ። ህዝቡን ያመነው አብይ አሕመድ አሸነፈ አለ። በመጨረሻም የግብፅ ህዝብ ሆይ አለ እውነታው ይሄ ነው ብሎ ተናዘዘ።

አልሸርቅ ቲቪ ላይ ከተናዘዘው የተወሰደ!!

ትርጉም በሱለይማን አብደላ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top