Connect with us

በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ነገ ለሕዳሴው ግድብ ከያሉበት ድምፃቸውን ያሰማሉ

በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ነገ ለሕዳሴው ግድብ ከያሉበት ድምፃቸውን ያሰማሉ
Photo: Social Media

ዜና

በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ነገ ለሕዳሴው ግድብ ከያሉበት ድምፃቸውን ያሰማሉ

ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ በያሉበት ሆነው ለሶስት ደቂቃ ደስታቸውን የሚያበስሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የሁነቱ አዘጋጆች “ድምጻችን ለግድባችን” በሚል መሪ ቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና ሊፍት ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ይህ ዓለም አቀፍ ሁነት ኢትዮጵያውያን ግድቡ አሁን የደረሰበት ደረጃ በመድረሱ የተሰማቸውን ደስታ እንዲገልጹ የተዘጋጀ ነው፡፡

የሊፍት ኢትዮጵያ መስራችና የቦርድ አባል አቶ አብርሃም ስዩም እንደተናገሩት፤ የግድቡ የመጀመሪያ ዙሪያ የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ እንደ ቀላል ነገር መታየት የለበትም፡፡ የዓለም ዐይንና ጆሮ የሚከታተለው እጅግ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በከፈለው መስዋዕትነት እና በመሪዎች ቆራጥ አመራር እዚህ መድረሱ እጅግ የሚያስደስት ነው፡፡

ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ደስታውን የሚገልጽበት መንገድ እየፈለገ ኮሮናን በመፍራት ሊያደርገው ስላልቻለ የህዝቡን ፍላጎት ለማሳካት ከጽህፈት ቤቱ ጋር በመሆን ሁነቱ መዘጋጀቱን ያብራሩት አቶ አብርሃም፤ በቤታቸው ያሉ ሰዎች በራፍ ላይ በመቆም፣ መኪና የሚነዱ ሰዎች መኪናቸውን ጥግ አስይዘው በማቆም፣ መንገድ ላይ የሚሄዱ ሰዎች ባሉበት ቆመው፣ ለሶስት ደቂቃ ደስታቸውን እንዲገልጹ ታስቦ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡

ነገ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የህዳሴ ግድብ ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ከሸራተን አዲስ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ መርሃ ግብር እንደሚኖርም ተጠቁሟል፡፡ #ኢፕድ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top