Connect with us

ህወሓት በትግራይ ምርጫ የሚሳተፋ ፓርቲዎችን ለውድድር ጋበዘ

ህወሓት በትግራይ ምርጫ የሚሳተፋ ፓርቲዎችን ለውድድር ጋበዘ
Photo: Facebook

ዜና

ህወሓት በትግራይ ምርጫ የሚሳተፋ ፓርቲዎችን ለውድድር ጋበዘ

ከቀሪው የአገሪቱ ክፍል በተለየ ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ በተወሰነበት በትግራይ ክልል ውስጥ በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲመዘገቡ ጥሪ እንደቀረበ ተገለጸ።

በቅርቡ በክልሉ ምክር ቤት የተቋቋመው የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ፓርቲዎች ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ ነሐሴ መጨረሻ ላይ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ በሙሉ ቀርበው እንዲመዘገቡ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

በጥሪው መሰረት በምርጫው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የግል ተወዳዳሪዎች ከዛሬ ማክሰኞ (ሐምሌ 21/2012) እስከ ሐሙስ (ሐምሌ 23/2012) ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ ሊመዘገቡ እንደሚችሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነ ማርያም ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ በምርጫው መሳተፍ ለሚፈልጉ ወገኖች ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ ከማቅረብ ውጪ ለምርጫው አፈጻጸም ስለሚያስፈልጉ የጊዜ ሰሌዳና ሌሎች ወሳኝ ነገሮች እስካሁን ያለው ነገር የለም።

ምርጫው ሊካሄድበት ይችላል ስለተባለው ትክክለኛ ቀንም እስካሁን የተገለጸ ነገር ባይኖርም ቢቢሲ ኮሚሽነሩን ስለዚሁ ጉዳይ ጠይቆ፤ ምርጫው የሚካሄድበት ቀንን ከሚመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር በመወያየት እንደሚወሰን መምህር ሙሉወርቅ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በክልላዊ ምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎችን ለምዝገባ ከመጥራት ውጪ፣ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ዝርዝር ነገሮች ምን ምን እንደሆነ አልገለፀም።(BBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top