Connect with us

ኃይሌ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የመኪና ስጦታ አበረከተ

ኃይሌ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የመኪና ስጦታ አበረከተ
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ኃይሌ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የመኪና ስጦታ አበረከተ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት የምትሠራ እና የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመች የመጀመሪያ መኪና ከአትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በስጦታነት ተቀብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሀዩንዳይ ፕሬዚደንት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የመገጣጠም ሥራ ተጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሠራውን እና የካርቦን ልቀት የማያስከትለውን መኪና በተቀበሉበት ወቅት፣ ይህን የመሳሰሉ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት የሚያስገኙ ሥራዎች በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለአረንጓዴ ልምላሜ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ይህን በኢትዮጵያ የተገጣጠመ መኪና ለየት የሚያደርገው፣ የተለየ የኃይል ማደያ ሳያስፈልግ በየትኛውም ቦታ ባትሪውን ለመሙላት መቻሉ ነው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top