Connect with us

እነታዬ ደንደአን አለማመስገን ንፉግነት ይሆናል!

እነታዬ ደንደአን አለማመስገን ንፉግነት ይሆናል!
Photo: Social Media

ትንታኔ

እነታዬ ደንደአን አለማመስገን ንፉግነት ይሆናል!

እነታዬ ደንደአን አለማመስገን ንፉግነት ይሆናል!
(ጫሊ በላይነህ)

ታዬ ደንደአ በአካል አላውቀውም፤ አያውቀኝም። እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በማህበራዊ ድረገፃች በተለይም በፊስቡክ የሚፅፋቸውን አጠር ያለ ደግሞ ጠጠር ሀሳቦቹን ከሚያደንቁት አንዱ ነኝ። ታዬ እንደተረዳሁት ከሆነ በዘመነ ወያኔ በእስርና መሳደድ ብዙ መከራን ተቀብሏል። ዛሬ የብልፅግና የኦሮምያ ፅ/ቤት የኮምኒኬሽን ኃላፊ መሆኑን ሰምቻለሁ።

በእኔ አተያይ የለውጡ ተግዳሮቶች የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች በአላማ ያልተቀደሰ ጋብቻ መመስረታቸው ነው። የውስጥ የሚባለው የብልፅግናን ከላይ እስከታች መዋቅር ግንባር ቀደሙ ነው። ጥቂት የማይባሉ አመራሮች የእነጀዋር መሐመድ አሽከሮች (ለቃል አጠቃቀሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ) ነበሩ። አንዳንዶቹም አጀንዳ አስፈፃሚ በመሆን በመላላክ ስራ ውስጥ ሲሳተፉ ቆይተዋል።

እነጀዋር አፋቸውን ሞልተው “የእኛ ሰዎች” በሚል መጠሪያ ለይተው የሚናገሩትም እነዚህ ግለሰቦች ባሳዩዋቸው ታማኝነት ነው። በተለይ ባለፈው ጥቅምት ወር “ተከብቤአለሁ” ማለቱን ተከትሎ መንግስት ባለበት ሀገር በጠራራ ፀሐይ መንጋዎቹ በመኪና ተጓጉዘው በዋና ከተማዋ አዲስአበባ ደጃፉን ሲያጥለቀልቁ እነዚህ ጥቂት ሹማምንት ዳር ቆመው ሲያጨብጭቡ ነበር።

እነዚህ ሞራለ ቢሶች በየቦታው በእሱ ጥሪ ምክንያት ከሞቱት፣ ከተጎዱት፣ ንብረታቸውን ካጡት ወገኖች ይልቅ አብዝተው ያለቅሱ የነበሩት “ጀዋር ተነካብን” በሚል ነበር። ስለህግ የበላይነት፣ ዜጎች በህግ ፊት ስላላቸው እኩልነት… እነዚህ ሰዎች ደንታ የሚሰጣቸው አልነበሩም። ዛሬ ቀን ሲጨልም እነዚሁ አስመሳይ ጥቂት ሹማምንት ቆዳቸውን ገፈው በተቃራኒው የህግ የበላይነት ተንታኝ እና አስፈፃሚ ሆነው ሲተውኑ ማየት በእጅጉ ይገርማል፤ ያማል።

ታዬ ደንደአ ግን ለእኔ ይለያል። የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሆኖም ከእውነት ጋር ብቻውን ቆሞ ሲሟገት ደጋግሜ አስተውያለሁ። እነጀዋር መሐመድን “እነግሪሳ”፣ “እነከበቡሽ”…እያለ በህግ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው በተደጋጋሚ በፌስቡክ ገፁ ፅፏል፤ ፊት ለፊት ሞግቷል። እንደኦነግ ሸኔ እና መቀለ የመሸገው ዘራፊ የህወሓት ስብስብ እንዲሁ የእናት ጡት ነካሽነታቸውን የሚያሳዩ የተለያዩ መጣጥፎችን ሲያቀርብ ቆይቷል።

እናም ምን ለማለት ነው?…ትላንት አጥፊዎችን ከባችሁ የልብ ልብ እንዲሰማቸው፣ በሰሩት ወንጀል ጭምር እንዲታበዩ ምክንያት የሆናችሁ እና ዛሬ ደግሞ ተከርብታሁ አውጋዥ፣ ህግ አስከባሪ መስላችሁ የቀረባችሁ የብልፅግና ጥቂት አመራሮች አሳምረን እናውቃችዃለን። አውቀንም ታዝበናችኸል። በቅርቡም ፓርቲው ለራሱ ሲል አራግፎ እንደሚገላገላችሁም ተስፋ እናደርጋለሁ።

በሌላ በኩል እንደታዬ ደንደአ ያሉትን የአደባባይ ታጋዮችን ግን አለማክበር፣ አለማመስገን ንፉግነት ይሆናል። ታጋዮቻችን ከፍ ያለ ክብር ይገባችሀል፤ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ስላደረጋችሁት ያልተቋረጠ ተጋድሎ እንደአንድ ኢትዮጵያዊ ምስጋናዬ ባላችሁበት ይድረሳችሁ!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ!!

 

 

 

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top