Connect with us

አስኮርቤትን በመጠቀም የኮቪድ-19ን ያልተገባ ሞት ማስቀረት ሲቻል

አስኮርቤትን በመጠቀም የኮቪድ-19ን ያልተገባ ሞት ማስቀረት ሲቻል
Photo: Social Media

ጤና

አስኮርቤትን በመጠቀም የኮቪድ-19ን ያልተገባ ሞት ማስቀረት ሲቻል

አስኮርቤትን በመጠቀም የኮቪድ-19ን ያልተገባ ሞት ማስቀረት ሲቻል
በአምኃየስ ታደሰ | amhayest@gmail.com

የኮቪድ-19 መንስኤ የተባለው ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሲነገራቸው ተስፋ የቆረጡት የአገራችን የሕክምና ዶክተሮች ስለ በሽታው ካላቸው የተዛባ ግንዛቤ አንፃር በእነርሱም ሆነ በመሰሎቻቸው ታክሞ የመዳን ተስፋ መኖሩ ያጠራጥራል፡፡ ምክንያቱም የኮሮና ቫይረሶች የሚያስከትሉት የመተንፈሻ አካል ችግር ከከባድ እንፍሉዌንዛ የበለጠ እንደማያሰጋ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ስለሚታወቅ ነው፡፡ በተጨማሪም ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል ለሕልፈተ-ሕይወት እየበቁ የሚገኙት በአማካይ ከዐ.3 በመቶ በታች መሆናቸው ሲታሰብ የምርመራ ውጤቱ በራሱ ተስፋ የሚያስቆርጥ መሆን አልነበረትም፡፡ ይልቁንም ጽኑ የሳንባ ጉዳት ካልተከተለ በስተቀር በየትኛውም የኮሮና ቫይረስ መያዝ በራሱ ለሞት እንደማይዳርግ ለመረዳት ሃኪም መሆንን አይጠይቅም፡፡

እንዱያም ሆኖ በየትኛውም ጽኑ የሳንባ በሽታ የሚቀጠፍ የሕሙማን ሕይወት ቢኖር የሃኪሞች የዘልማድ አስተሳሰብ ብሎም ድንቁርና ውጤት እንጂ በሌላ ምክንያት እንዳልሆነ በሕያው ምስክር ገጠመኝ ላስረግጥ፡፡ ታሪኩን በጽሁፉ ግርጌ ካለው የዩቲብ ቪዲዮ ዘገባ መገንዘብ የሚቻለው ኒው ዚላንዳዊው ገበሬ አላን ስሚዝ በጽኑ የሳምባ ምች ምክንያት ኦክላንድ ሆስፒታል ተኝቶ ለመታከም የተገደደው በ2ዐዐ1 ዓ. ም. ነበር፡፡ የ56 ዓመቱ እንስሳት አርቢ ምግብ መውሰድ በማቆሙ ክብደቱ 33 ኪሎ ግራም ከመቀነሱ በተጨማሪ በስዋይን ፍሉ የተጠቃው ሳንባው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እንደሆነ በግራ በኩል ካለው የኤክስ-ሬይ የምርመራ ውጤት መረዳት ይቻላል፡፡

በተጨማሪም በምስሉ ከላይ እንደተመለከተው ሚስተር አላን ሠው-ሰራሽ የመተንፈሻ መሣሪያ (ኤክሞ) ተገጥሞለት፣ ዘመኑ ያፈራውን መድሃኒት ከግሉኮስ ጋር እየወሰደ በጤናው ላይ ለውጥ ባለመታየቱ እለተ ሞቱን ከመጠበቅ ውጪ ለሃኪሞቹ አማራጭ አልታያቸውም፡፡ በተጨማሪ የደም ካንሰር እንዳለበት የሚታወቀው ይኸው ታካሚ የመትረፍ እድሉ ተሟጥጦ ሙሉ በሙሉ ራሱን ከመሳቱ አንፃር በፅኑ ሕክምና መስጫ ማዕከል ውስጥ የተገጠመለት ቬንቲሌተር መሰል አርተፊሻል የመተፈንፈሻ መሣሪያ ተነቅሎ ሕይወቱ እንድታልፍ የሆስፒታሉ ሃኪሞች በአንድ ድምጽ ይወስናሉ፡፡ በአገሪቱ ሕግ መሠረት ዶክተሮቹ የደረሱበትን የሙት በቃ ፍርድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚቀራቸው የቤተሰቦቹን ይሁንታ ማግኘት ብቻ ነበር፡፡

በአንፃሩ በአባታቸው እስትንፋስ ተስፋ ያልቆረጡት የሚስተር ስሚዝ ልጆች ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ሲ ወይም አስኮርቢክ አሲድ (አስኮርቤት) በደም ስር ቢሰጠው ሕይወቱ እንደሚተርፍ እንደሚያምኑ በመግለጽ ያልተጠበቀ አማራጭ ይዘው ወደ ሆስፒታሉ ይቀርባሉ፡፡ ሃኪሞቹ ሰምተው በማያውቁት የቫይታሚን ሲ ሕክምና የተፈወሰ ታካሚ እንደሌለ በመግለጽ የገበሬውን እስትንፋስ ከማቋረጥ ውጪ ሌላ ሙከራ በማድረግ በከንቱ መድከም እንደማይፈልጉ በያዙት አቋም ይፀናሉ፡፡ በአጋጣሚ ከጥቂት ማቅማማት በኋላ ከ8ቱ ሃኪሞች አንዱ ቤተሰቦቹን ለማስደሰት ብቻ በኃሳቡ በመስማማቱ ልጡ ወደ ተራሰለትና ጉድጓዱ የተማሰለት የሚስተር አለን በድን በቀን 5ዐ,ዐዐዐ ሚሊግራም (5ዐ ግራም) አስኮርቢክ አሲድ በደም ስር መሰጠት ተጀመረ፡፡

የቫይታሚን ሕክምናው በተጀመረ በማግስቱ የኤክስ-ሬይ ምርመራው በሳምባው ላይ ያልተጠበቀ ለውጥ ማሳየቱ ቢታወቅም የሚስተር ስሚዝን ቤተሰቦች ተስፋ የሚያጨልም ሌላ ደንቃራ መፈጠሩ ግን አልቀረም፡፡ በተለይም ሃኪሞቹ በደም ስር ይሰጠው የነበረውን የአስኮርቤት መጠን ከ5ዐ,ዐዐዐ ሚሊግራም (5ዐ ግራም) ወደ 2,ዐዐዐ ሚሊግራም (2 ግራም) በመቀነስ ገበሬውን ለመግደል ያደረጉት ሙከራ ጠበቃ እስከመቅጠር በደረሱት የቤተሰቦቹ ጥረት ባለመሳካቱ ዛሬ ሞትን ድል እንደነሳ የሚናገረው ሚስተር ስሚዝ ከሆስፒታል ለመውጣት የፈጀበት ተጨማሪ 13 ቀናት ብቻ ነበር፡፡ እጅግ የሚደንቀው ሂደቱን በቅርበት ይከታተሉ በነበሩት ዶክተሮች ዘንድ ጭምር ክስተቱ እንደ ተአምር ወይም በህክምና ቋንቋ ስፖንታንየስ ሪሚሽን ተደርጐ ይቆጠር እንጂ የቫይታሚን ሲ ወደር የለሽ ፈዋሽነት በሚስተር ስሚዝ የተወሰነ እና የአጋጣሚ ውጤት አይደለም፡፡

ይልቁንም የበሽታ መከላከል ስርአታችን ያለአስኮርቢክ አሲድ ፋይዳ እንደሌለው በማስገንዘብ የሚታወቁት እስከ ዛሬ ድረስ ሁለት የኖቤል ሽልማቶችን ያለተካፋይ ወይም በብቸኝነት መውሰድ የቻሉት ብቸኛው የምድራችን ሳይንቲስት ዶ/ር ላይነስ ፖሊንግ ናቸው፡፡ ከአርባ ስምንት የተለያዩ የዓለማችን ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው ዶ/ር ፖሊንግ ቫይታሚን ሲ ዘ ኮመን ኮልድ ኤንድ ዘ ፍሉ በሚል መጽሃፋቸው ማንኛውም ሰው ቢያንስ በቀን 1,ዐዐዐ ሚሊግራም (1 ግራም) አስኮርቢክ አሲድ በየዕለቱ ቢወስድ ሁሉንም የመተንፈሻ አካል ሕመም መከላከልና ለበሽታ የመጋለጥ ዕድል ቢኖር እንኳን ቶሎ ማስወገድ እንደሚችል ያስታወቁት በ1962 ዓ. ም. ነበር፡፡

ዶ/ር ፖሊንግ አስኮርቤት በተለይ ኘሮቲኖችንና ሊፒዶችን ከኢንፌክሽን ጋር ተያይዞ ከሚከሰት የፍሪ ራዱካልስ ጉዳት በመታደግ ለሕዋሳት ጤናማነት የማይተካ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል፡፡ በርግጥም የቫይታሚን ሲ የሳንባ የጤና ችግሮች ፍቱንነት መታወቅ የጀመረው ዶክተር ፍሬድሪክ ክሌነር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተመለሱ በኒሞንያ የተጠቁ 42 የአሜሪካ ወታደሮችን አስኮርቤት በደም ስር በመስጠት በጥቂት ቀናት ውስጥ መፈወስ ከቻሉበት ጊዜ አንስቶ ነበር፡፡ ዶ/ር ክሌነር በተለይ ሰውነትን ከወራሪ በመከላከል የሚታወቁት የነጭ የደም ህዋሳት ማለትም ሊዩኮሳይትስ የቫይረስ ጥቃት ወይም ጉዳት ወደ ደረሰበት የአካል ክፍል ሲዘምቱ የቫይታሚን ሲ ፍጆታቸው እንደሚጨምር ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡

አስኮርቤት በፀረ-ወክሳጅነት ባዮሎጂያዊ ዝገትን በመቀነስ፣ የመተንፈሻ አካል ክፋዮች የሆኑትን ኮላጅኖች ምርት በማሳደግ፣ ሊዩኮሳይቶች በቀላሉ በሽታ አምጪዎችን እንዲፋለሙ በማገዝ እና እንደ ፀረ-ሂስታሚን በማገልገል ጭምር ከፀረ-ቫይረሶችም ሆነ ፀረ-ተውሣኮች የላቀ አስተዋፃኦ እንደሚያደርግ የሕክምና ምርምር ውጤቶች በማያሻማ ሁኔታ አረጋግጠዋል፡፡ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ አቀንቃኞቹ የመገናኛ ብዙሃን ባይዘገብም ቻይና የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር የቻለችው የአገሪቱ መንግስት ዲኤስኤም የተባለ የኔዘርላንድ ኩባንያ 5ዐ ቶን ቫይታሚን ሲ እንዲያቀርብ ማድረጉን ተከትሎ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከቻይና በተጨማሪ በጣሊያን፣ ደቡብ ኮርያ፣ ጃፓን እና አሜሪካ ጭምር በደም ስር በከፍተኛ መጠን እየተሰጠ የሚገኘው ቫይታሚን ሲ በአገራችንም ለሕሙማኑ እንዲደርስ መደረጉ የሚበረታታ ቢሆንም በቀን 1,ዐዐዐ ሚሊግራም (1 ግራም) መሆኑ የተገለጸው የአስኮርቤት መጠን ግን በፍጥነት እንዲያገግሙም ሆነ እንዲፈወሱ የሚያስችል አይደለም፡፡

ለአብነትም ቻይና ውሃን ከተማ የሚገኘው ዞንግናን ሆስፒታል እስከ 24,ዐዐዐ ሚሊግራም (24 ግራም) የሚደርስ አስኮርቤት በደም ስር እንዲሰጥ የሚያደርግ ሲሆን ወደ ዚያን ጃያኦቶንግ ሆስፒታል የገቡ ሕሙማንም በቫይታሚን ሲ ብቻ በፍጥነት ማገገማቸውን ዩኒቨርሲቲው በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡ የሻንጋይ ግዛት መንግስትም እስከ 16,000 ሚሊግራም (16 ግራም) አስኮርቢክ አሲድ ለኮቪድ-19 ተጠቂዎች እንዲሰጥ የሻንጋይ ኘላን የተባለውን በይፋ ያጸደቀው በ3ዐዐ ሕሙማን ላይ ከተደረገው ስኬታማ ሕክምና በመነሳት እና በቁጥር 3ዐ የሻንጋይ ሜዲካል ማኀበር አባል የሆኑ ኤክስፐርቶች ያቀረቡትን የውሣኔ ኃሳብ ተከትሎ ነው፡፡

ዴኤጐ ክልል የሚገኝ የደቡብ ኮርያ ሆስፒታል 30,ዐዐዐ ሚሊግራም (3ዐ ግራም) አስኮርቤት በደም ስር በመስጠት አብዛኛው የኮቪድ-19 ሕሙማን በሁለት ቀናት ውስጥ እንደተሻላቸው ያረጋገጠ ሲሆን ጃፓን ለቫይረሱ ተጠቂዎች የምትሰጠው የሕክምና ኘሮቶኮልም ከ3,ዐዐዐ ሚሊግራም (3 ግራም) በደም ስር የሚሰጥ ቫይታሚን ሲ በተጨማሪ ሌሎች ደቂቅ ንጥረ ምግቦችን ያካተተ ነው፡፡ በኒው ዮርክ ግዛትም 23 ሆስፒታሎች በየእለቱ 6,0ዐዐ ሚሊግራም (6 ግራም) የተሰጣቸው የኮቪድ-19 ሕሙማን አስኮርቤት ካላገኙት ሌሎች መሰሎቻቸው ጋር ሲነፃፀር ስቃያቸው ከመቀነስ አንስቶ በጤንነታቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን ዶ/ር አንድሪው ዌበር የተባሉትን የመተንፈሻ አካላት እና የጽኑ ህክምና ስፔሻሊስት በመጥቀስ የዘገበው ኒው ዮርክ ፖስት ነው፡፡

ዶ/ር ዌበር ቫይታሚን ሲ ሰውነት ለቫይረሱ ጥቃት ምላሽ ሲሰጥ ከተጋነነ ብግነት ወይም ኢንፍላማቶሪ ኦቨርሪአክሽን የተነሳ የሚከሰተውን ሴኘሲስ እንደሚከላከል እና በደም ውስጥ የሚኖረው የአስኮርቤት መጠን በዚሁ ምክንያት በእጅጉ እንደሚያሽቆለቁል በማረጋገጥ ከፍተኛ መጠን ያለው አስኮርቢክ አሲድ በመላው ዓለም ለኮቪድ-19 ሕሙማን ቢሰጥ ያልተጠበቀ ለውጥ እንደሚታይ መጥቀሳቸው ተያይዞ ተገልጿል፡፡ እዚያው አሜሪካ ሲያትል ውስጥ በኤስሲ ቫይረስ መያዛቸው የታወቀው ዶ/ር ርያን ፓድጌት እና ዶ/ር ጄፍ ብራውን የተባሉት የቨርጂኒያ ሃኪምም ከኮቪድ-19 መፈወስ የቻሉት በዘልማዱ ሕክምና ሳይሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ሲ በደም ስር ከወሰዱ በኋላ መሆኑን መጥቀስ እዚህ ላይ ተገቢ ነው፡፡

በሌላዋ የቴክሳስ ሃውስተን ደግሞ የከፋ የኒሞኒያ ችግር የነበረባቸው የኮቪድ-19 ሕሙማን በደም ስር አስኮርቤት ሲሰጣቸው ከበሽታቸው በማይታመን ፍጥነት ማገገማቸውን በተለይም በዩናይትድ ሚሞርያል ሜዲካል ሴንተር እስካሁን የተመዘገበው ሞት ዜሮ መሆኑን በመግለጽ ዶ/ር ዮሴፍ ቫሮን ውጤቱን ሰዎች ለመቀበል እንደሚቸገሩ አምናለሁ፤ እመኑኝ ቫይታሚን ሲ ይፈውሳል ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ ከስኬታማ ተሞክሮዎች መረዳት የሚቻለው የሕሙማኑ የጤና ሁኔታ ብሎም በደማቸው ውስጥ የሚገኘው የአስኮርቤት መጠን እየታየ በየቀኑ ከ4,ዐዐዐ ሚሊግራም (4 ግራም) ያላነሰ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በአንድ ኪሎግራም ክብደታቸው 2ዐዐ ሚሊግራም (0.2 ግራም) ታስቦ በሰዓታት ተከፋፍሎ በደም ስር ቢሰጣቸው በአጭር ቀናት ውስጥ ሕክምናቸውን አጠናቅቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸው የማያጠራጥር መሆኑን ነው፡፡ እንዲሁም የችግሩ ተጠቂ የሆኑ ሕፃናት በታፋቸው በቀን እስከ 2,ዐዐዐ ሚሊግራም (2 ግራም) የሚደርስ አስኮርቢክ አሲድ ቢያገኙ በጤናቸው ላይ የሚኖረውን ለውጥ በጥቂት ቀናት ውስጥ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ከቫይታሚን ሲ በተጨማሪ ሕሙማኑ በቀን እስከ 1,6ዐዐ ማይክሮግራም ያህል ሴሌንየም፣ 25 ሚሊግራም ዚንክ፣ 1,ዐዐዐ (1 ግራም) ሚሊግራም ማግኒዚየም እና 5,ዐዐዐ ኢንተርናሽናል ዩኒት (አዩ) ቫይታሚን ዲ3 በየዕለቱ ቢያገኙ የተለየ የጤና ችግር ቢኖርባቸው እንኳን ለሕልፈተ ሕይወት የመዳረግ ስጋት ፈጽሞ አይኖርባቸውም፡፡ እውነታው ይኽ ሆኖ እያለ የቫይታሚን ሲን አስተማማኝ የመፈወስ ብቃት ያስመለከተው መረጃ ከሃኪሞች ሊሰወር የቻለው እነሱ የሰለጠኑት በዋንኛነት ፋርማሲያዊ መድሃኒቶችን ለማሻሻጥ እንጂ ለሕሙማን የጤና ችግር የተሻለውን መፍትሄ እንዲያቀርቡ በሚያስችል መንገድ ባለመሆኑ የተነሳ ነው፡፡

ለአብነትም የአሜሪካ ብሄራዊ የጤና ተቋም ሹመኛ እንዲሁም የኮቪድ-19 የሃይማኖት መሪ የሆነው ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ ሳንባ ነክ ወረርሽኝ ሲከሰት ለራሱ በየእለቱ እንደሚወስድ በአጋጣሚ የገለጸውን 1,ዐዐዐ ሚሊግራም (1 ግራም) ቫይታሚን ሲ ቫይረሱ ለተገኘባቸው ሕሙማን እንዲሰጥ ሲመክርም ሆነ ዶክተሮች ለውስጥ ደዌ ሕክምና በሚያጣቅሱት በእርሱ ኤዲተርነት በሚዘጋጀው የሃሪሰንስ ኘሪንስኘልስ ኦፍ ኢንተርናል ሜድስን መጽሃፍ ውስጥ እንዲካተት አላደረገም፡፡ በተጨማሪም ፓተንት የሚደረጉ መድሃኒቶችን በመጠቀም በበሽታ የሚነግዱት ፋርማሲያዊ ኩባንያዎች የመረጃ ምንጮቻችንንም ሙሉ-በሙሉ በመቆጣጠራቸው እንድናውቅ ያደረጉን እነሱ የሚፈልጉትን እንጂ ለእኛ የሚጠቅመንን አይደለም፡፡

ለዚሁ ዋቢ የሚሆነው በቅርቡ ዩቲዩብ ለተመልካች እንዳይቀርቡ ወይም እንዲወገዱ ከሚደረጉት ቪዲዮዎች መካከል ኮቪድ-19 በቫይታሚን ሲ ይፈወሳል የሚሉት እንደሚገኙበት የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሱዛን ወጂሲኢኪ መግለጿ ነው፡፡ ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምም የዩቲዩብ ድርጊት ቫይታሚን ሲ ለኮቪድ-19 ሕክምና እንዲውል ከሚደነግገው ድርጅታቸው መጋቢት 12 ቀን 2ዐ12 ዓ. ም. ይፋ ካደረገው የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ምርምር ፍኖተ-ካርታ አቋም ጋር የሚቃረን እንደሆነ በመግለጽ ሲከራከሩ አልተሰሙም፡፡

በዚሁ አጋጣሚ እስካሁን ለኮቪድ-19 ምላሽ 4 ቢሊዮን ብር በጀት የመደበው የአገራችን መንግስት በተለይም የጤና ሚኒስቴር ከአስከሬን ምርመራ በመነሳት በሌሎች በሽታዎች የሞቱትን ጭምር ከወረርሽኙ ሰለባዎች በመቁጠር ዜጐችን ከማሸበር ይልቅ የሕክምና ኘሮቶኮሉን በማስተካከል ቫይረሱ የተገኘባቸውም ሆነ ሌሎች የንጥረ ነገሩ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ቢያመቻች ይበልጥ ውጤታማ እንደሚሆን ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡ በተጨማሪም አጋጣሚው ገበያ የፈጠረላቸው በተለይም በመድሃኒት ማስመጣት እና ፍብረካ የተሰማሩ ተቋማትና ግለሰቦች አንድም ወገናችን ላልተገባ ሕልፈተ ሕይወት እንዳይዳረግ በቫይታሚን ሲ አቅርቦት ጭምር ቢሳተፉ ከሚጠብቁት የተትረፈረፈ ትርፍ ይልቅ የሞራል ግዴታቸውን መወጣታቸው የበለጠ እርካታ እንደሚያስገኝላቸው አምናለሁ፡፡

በመጨረሻም ዶክተር ላይነስ ፖሊንግን በቫይታሚን ሲን አስመልክቶ በያዙት አቋም ላይ ከብዙሃኑ የሕክምና ማኀበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲገጥማቸው “የጤና አጠባበቅ ሹማምንትም ሆኑ ፖለቲከኞች በተሳሳተ አቅጣጫ እንዲመሩህ አትፍቀድላቸው” ለማለት መገደዳቸውን በማስታወስ የምሰናበተው ከሳኒታይዘር ወይም ማስክ በተሻለ መንገድ ከኮቪድ-19 ስጋት ነፃ ከማድረጉ አንፃር የአስኮርቤት ፍጆታን በየቀኑ ማሳደግ የአንባብያንም መደበኛ ተግባር ቢሆን እንደሚመረጥ እንደሚገባ በማሳሰብ ነው፡፡

ለጽሁፌ በተለይ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በመጋራት መረጃ ለሰጡኝ ቻይናዊ አሜሪካዊ የኦርቶሞሎኪዩላር ሕክምና ጠቢብ ዶ/ር ሪቻርድ ቼንግ ምስጋናዬን እያቀረብኩ በመግቢያው ላይ ታሪኩ ስለተጠቀሰው የአላን ስሚዝ የቫይታሚን ሲ ሕክምና ይበልጥ ለማወቅ የሚፈልጉ የሚከተለውን የዩቲዩብ ቪዲዮ መመልከት እንደሚችሉ እጠቁማለሁ፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top