Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡን ሸጠውታል

ሌላው ቀርቶ ዶክተር አብይም መንግስት የለም ብትል አንሰማህም ትመራናለህ፤ ትመራናለህ፡፡ከፍቅሩ ምስጋናው
Photo: AP

ትንታኔ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡን ሸጠውታል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡን ሸጠውታል፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ገዝተንዋል፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ

ዶክተር አብይ የታላቁ ህዳሴ ኢትዮጵያ ግድብን መሸጣቸው ሲነገር ሰንብቷል ሰውዬው በእርግጥም አድርገውታል፡፡ ግድቡን ለኢትዮጵያውያን መሸጣቸውን ግብጻውያን አረጋግጠዋል፡፡ ዶክተሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ የሚታሙበት ነገር ቢኖር እንኳን ሀገርን በመጥላትና ኢትዮጵያን በመጉዳት ስማቸው ሊነሳ የማይገባ መሪ ነበሩ ግን መስከረም ሳይጠባ ጉድ ሰማን፤ ሰውዬው በግድብ ሽያጭ ታሙ፡፡

የታሙትን ሆነው የማያውቁ ሰው ናቸው፡፡ እዚያ ጎጠኛ ሲሏቸው አዘነበሉለት በተባሉት ጎጥ ደግሞ አሳሪና ገራፊ የሚል ስም ይወጣላቸዋል፡፡ ስመ ብዙው ጠቅላይ ሚኒስትር ከስማቸው የገጠመው ግድብ ሻጭነታቸው ነው፡፡ እውነትም እንደ ታሙት ግድቡን ለኢትዮጵያውያን ሸጡት፡፡

አንዳንዶች የፖለቲካ ኩርፊያ ስህተት አስመኛቸው ክፋት አስቃዣቸው፡፡ ግድቡ በዲፕሎማሲ ከስሮ ኢትዮጵያ አንገቷን ስትደፋ ለመመልከት የቋመጡም ነበሩ፡፡ ከዚያም ሲያልፍ ደግሞ የግብጽን ጦር ሃያልነት የነገሩን የሀገራችንን ጉድ መግባት ያረዱን ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያ ሰው እንዳለው ሳይሆን በፈጣሪ እንደታሰበላት መልካሙ ገጠማት፡፡

በየምስራቹ ዋዜማ ሞት ነበር፡፡ ስቆቃው ከዳር ዳር አስተጋብቶ ከግድቡ ቀድሞ ምድሪቷ በተጎዱ ሰዎች እንባ ተሞልታ ነበር፡፡ ይሄ ሁሉ ስቆቃ ነገን ማየት ላልቻለ የኢትዮጵያ መጨረሻ መስሎት ነበር፡፡ የሞት ድግስ በሀገራችን ሰማይ ሲያንዣብብ የሰው ስጋ የሚበላው አሞራ ፖለቲካችን ራሱን አመቻቸ፡፡ ከሰረች የተባለችው ኢትዮጵያ ሁሉን አክሽፋ በድምቀት ተገለጠች፡፡

ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን በራሳችን ገንዘብ የገነባነውን ግድብ ከራሳችን መሪ የገዛን መሪያችን ለራሳችን የራሳችንን የሸጠልን፤ አሳልፎ ሰጠ የተባለው አልፈን የምንበለጽግበትን እውን ያደረገ ስራ የሰራበትን ድል አብረን አከበርን፡፡ አንድ ላይ የጀመርነውን ግድብ አንድ ላይ እንጨርሰዋለን፡፡

ፖለቲካ ጥቅም እና ራስ ወዳድነት የነዳቸው በራሳቸው መንገድ ይሂዱ መድረሻቸው ሀፍረት ነው፡፡ ትናንት ግድቡን በፖለቲካ ኩሪፊያቸው ሳቢያ የጠላት ሀሳብና ስራ ያደረጉት ነበሩ፤ ዛሬ ስፍራው ተቀያይሯል፡፡ ትናንት ለግድቡ እንሞታለን ያሉት ዛሬ ምን አገባኝ ባይነታቸው ጥግ ደርሶ ጭራሽ ድል የተጎናጸፍንበትን ፕሮጀክት መርዶ ሊያደርጉት ሞክረዋል፡፡ እንደ አለቀለት ያወሩለት ግድብ የፍጻሜው ድል ጅማሮ ታይቷል ግድቡም ውሃ መያዝ ጀምሯል ከሚለው የተንጠለጠለ ዜና ተላቆ እንኳን ደስ ያላችሁ የመጀመሪያው ዙር ሙሌት በድል ተጠናቋል የሚለውን ሰምተናል፡፡

ግድቡን በመሸጥ የታሙት ጠቅላይ ሚኒስትርም ለካስ የገዛቸው ህዝባቸው ኖሯል፡፡ እንኳን ሸጡት እንኳን ገዛናቸው፡፡

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top