Connect with us

የዘገየው የ 40 በ60 ቤቶች የቁልፍ ርክክብ ተጀመረ

የዘገየው የ 40 በ60 ቤቶች የቁልፍ ርክክብ ተጀመረ

ዜና

የዘገየው የ 40 በ60 ቤቶች የቁልፍ ርክክብ ተጀመረ

~ የ13ኛ ዙር የኮንደምኒየም ዕድለኞች ቤታቸውን መቼ እንደሚረከቡ አልታወቀም

እጅግ የዘገየው የ2ኛ ዙር የ40 በ60 የመኖሪያ ቤቶች የቁልፍ ርክክብ ከትላንት ሐምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተጀመረ።
የቁልፍ ርክክቡ ምንም እንኳን የዘገየ ቢሆንም ያነጋገርናቸው አንዳንድ ዕድለኞች ተስፋ እና ትግእስታቸው በተሟጠጠበት ወቅትም ቢሆንም ቤታቸውን ትረከባላችሁ በመባላቸው ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የወጣባቸውና በጠቅላላ 20/80 ጨምሮ ከ32 ሺ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ናቸው።
ዕጣው በወጣበት ወቅት ቤቶቹ የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል እንደሆነ በመግለጽ ውዝግብ በመነሳቱና ቤቶቹን ማስተላለፍ ባለመቻሉ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተነሳውን የውዥንብርና ውዝግብ በማጥናት፣ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭምር ትዕዛዝ መሰጠቱ የሚታወስ ቢሆንም፣ ከአንድ ዓመት በላይ ግን ለሕዝብ ምንም የተገለጸ ነገር አልነበረም፡፡

ኮሚቴው ባደረገው ጥናት ዕጣ ከወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 9 ሺ ቤቶች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መገንባታቸውን አረጋግጦ፣ ለአስተዳደሩና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ማቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ በቅርብ ዘግቦ እንደነበር ይታወሳል። በመሆኑም በከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ተረፈ ፊርማ ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ከወራት በፊት የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለፈው መጋቢት ወር ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች ይተላለፋሉ ቢባልም ባልታወቀ ምክንያት እስካሁን ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።

ይህም ሆኖ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን ላይ የተገነቡ ቤቶች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን እስካሁን በይፋ የሚታወቅ ነገር አለመኖሩ አሳሳቢ ከመሆኑም በተጨማሪ የቤቱ ዕድለኞች ዘወትር ጥያቄ የሚያቀርቡበትና ተገቢውን ምላሽ የተነፈጉበት ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ውዝግብ የተነሳባቸው እንደኮዬ ፈጪ ባሉ አካባቢዎች የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር በልማት ምክንያት ለሚነሱ ወገኖች ቤት እየሰጠ እና የተረከቡም ተነሺዎች ወደቤቶቹ ገብተው በመኖር ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። ይኸም ሆኖ ለ13ኛ ዙር የኮንደምኒየም ዕድለኞች ቤቶቹ ሳይሰጡ የዘገዩበት ተጨባጭ ምክንያት አለመታወቁ አሁንም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top