Connect with us

በማህበራዊ ሚዲያዎች የጥላቻ ንግግርን የሚያስቆም ኔትዎርክ ተቋቋመ

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግርን የሚያስቆም ኔትዎርክ ተቋቋመ
Photo: Social Media

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

በማህበራዊ ሚዲያዎች የጥላቻ ንግግርን የሚያስቆም ኔትዎርክ ተቋቋመ

በማኅበራዊ ሚዲያና በሌሎች መደበኛ መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚሰራጩ ጥላቻንና ጥቃትን የሚያበረታቱ መልዕክቶችን ለማስቆም በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አንድ ኔትወርክ አቋቁመዋል።

ነዋሪነታቸው በአሜሪካ የሆነውና የዚህ እንቅስቃሴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ነአምን ዘለቀ እንደተናገሩት ኔትወርኩ በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀሩ ኮሚቴዎችን የያዘ ነው።

ኮሚቴዎቹ የሕግ፣ የሚዲያና ዲፕሎማሲ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ዘርፍ የተዋቀሩ ናቸው።

ይህ ኔትወርክ በአሜሪካ፣ በካናዳና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ያሉ በርካታ የፖለቲካ ሰዎች፣ ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ ሲቪክ ማኅበረቦች የተሰባሰቡበት እንደሆነም አቶ ነአምን ጨምረው አስረድተዋል።

ኔትወርኩ በአገር ውስጥ መረጋጋት እንዲመጣ የሕግ የበላይነት እንዲከበር፤ ወንጀለኞችና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ ለሕግ እንዲቀርቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስተባባሪው ገልፀውልናል።

የማኅበራዊ ሚዲያው ኮሚቴ ‘ተጋምደናል’ (Interunited) የሚል ዘመቻ የጀመረ ሲሆን የጥላቻ ንግግሮችን በመሰብሰብና ሪፖርት በማድረግ እንዲሁም ባሉት ገፆች አማካይነትም መልዕክቶችን የማስተላለፍ ሥራ ይሰራል።

ምንጭ፣ናትናኤል መኮንን

Continue Reading
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top