Connect with us

ዐብይን መደገፍ የምርጫ ጉዳይ አይደለም

ዐብይን መደገፍ የምርጫ ጉዳይ አይደለም
Prime Minister Abiy Ahmed of Ethiopia said the choice was simple: The dam, seen by his government as crucial for development, must either be filled or demolished. He has vowed to fill it.Credit...Michael Tewelde/Agence France-Presse — Getty Images

ትንታኔ

ዐብይን መደገፍ የምርጫ ጉዳይ አይደለም

ዐብይን መደገፍ የምርጫ ጉዳይ አይደለም
(ጫሊ በላይነህ)

ዶ/ር ዐብይ አሕመድ በሳል ፓለቲከኛ ነው። የ60ዎቹን ፓለቲካ ላለመድገም ባለፉት ሁለት ዓመታት ላቡን ዘርቷል።

ይኸን ሁሉ የሞከረው በከባድ አጣብቂኝ ውስጥ ሆኖ ነው። በሀገር ውስጥ በሕዝብ ተቃውሞ ከመንበረ ሥልጣኑ የተባረረው ህወሓት የመቀለ ምሽጉን ካደላደለ በኃላ ኢላማውን ያስተካከለው ዐብይ ላይ ነው። ራሱን የኦሮሞ ተገንጣይ ነኝ ያለው ቡድን በምእራብ ኦሮምያ ጫካዎች እየተሹለከለከ ንፁሀንን የሚገድለውና የሚያሳድደው የዐብይን አስተዳደር እቃወማለሁ በሚል ነው።

በተፈጠረው ለውጥ የኢትዮጵያን ምድር የረገጡ አንዳንድ የኦሮሞ ልሂቃን ለውጡ በሰጣቸው እድል ውስጥ ተጠልለው ዐብይን “ዲቃላ” በማለት እስከመዝለፍ ድፍረት ከማግኘት አንስቶ እንመራዋለን የሚሉትን በኘሮፖጋንዳቸው የተታለለ የኦሮሞ ወጣት ለጥፋት እስከማሰማራት የደፈሩት የዐብይን መንግስት በመቃወም ስም ነው።

በውጭ በአባይ ጉዳይ ሁሉንም አማራጭ መንገዶች አሟጣ የምትጠቀመው ግብፅ ዶላሯን በማፍሰስ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ የገባችው በዐብይ መንግስት ላይ ጥርስ በመንከሷ ነው።

እነዚህ ሀይሎች ከመቃወም አልፈው ለጥፋት ሲናበቡና አንዳንድ የሚታዩ ጥፋቶችን ሲፈፅሙ የዐብይ አስተዳደር በሆደሰፊነት ብዙ ታግሷል። ይኸን ጥፋት ለማስታገስ የሚወሰድ እርምጃ አምባገነንነትን ያመጣል በሚል ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ ቆይቷል።

ግን በዝምታ ነገሩን መፍታት የማይቻል ሆነ። ነውጠኞች ዝምታውን በፍርሀት ሚዛን ላይ አስቀምጠውት የልብ ልብ ተሰማቸው።ሀገርና ሕዝብ ጠባቂ ያጡ ይመስል በጠራራ ፀሐይ ሞት እና ውድመትን መጎንጨት ግድ ሆነባቸው።

የዶ/ር ዐብይ አሕመድ አስተዳደር ሳይወድ በግድ በሀይል ሕግና ሥርዐትን ማስከበር፣ ዜጎችን ከተጨማሪ ጥቃት ለመጠበቅ ተገደደ። እንግዲህ ንፁሀንን አራጅ፣ ንብረት አውዳሚ ሀይልን ለማስታገስ ሀይል መጠቀም ግድ ሆነ።

እኛም ሀገር በአጣብቂኝ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት መሪያችንን በርታ፣ የደፈረሰውን አጥራ በማለት ከጎኑ መቆም ግዴታችን ሆኗል። አዎ! መንጋውን አደብ ለማስገዛት በአንድ ሆነን ከመቆም የተሻለ አማራጭ የለንም።

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top