Connect with us

ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የእስር ቤቶች መጨናነቅ አሳስቦታል

ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የእስር ቤቶች መጨናነቅ አሳስቦታል
Photo: Social Media

ጤና

ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የእስር ቤቶች መጨናነቅ አሳስቦታል

ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የእስር ቤቶች መጨናነቅ አሳስቦታል

( ጋዜጣዊ መግለጫው እነሆ)

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን የሰብዓዊ መብት ሁኔታን በሚመለከት ከግንቦት 12-17 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኙ የተመረጡ ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤቶች ፈጣን የመስክ ምልከታ እና ክትትል ማከናወኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በክትትሉ የእስረኞችን ቁጥር መቀነስን ጨምሮ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ በማረሚያ ቤት ወይም በፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ፣ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ መንግስት ለወሰዳቸው እርምጃዎች ኢሰመኮ እውቅና እንደሚሰጥ ተገልጧል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽኑ በተደረገው ክትትል ከዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መርሆች እና ደረጃዎች አንፃር አሁንም አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ስጋቶች መኖራቸውን ተመልክቷል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በማረሚያ ቤቶችም ሆነ በፖሊስ ጣቢያዎች ቀድሞ የነበረው መጨናነቅ በተወሰነ መጠን ቢቃለልም፤ አሁንም ያለው የእስረኞች ብዛት እና የቦታው አለመመጣጠን ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት አስጊ መሆኑን መመልከቱ ይገኝበታል፡፡

ኮሚሽኑ በአስቸኳይ ሊተገበሩ ይገባል ያላቸውን ምክረ ሀሳቦች በማከል የክትትል ሪፖርቱን ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስት አካላት እና ተገቢውን እገዛ ለማድረግ ለሚችሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መላኩን አስታውቋል፡፡

በሪፖርቱ ላይ እንደተመለከተው በዚህ የኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በእስር ላይ ያሉ ሰዎች በራሳቸው ውሳኔ አካላዊ ርቀትን የመጠበቅና በጤና ባለሙያዎች የሚመከሩ የንፅህና እና የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማግኘት እድላቸው ውስን በመሆኑ፤ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመጠበቅ ካለበት ሀላፊነት አንፃር ተገቢውን እና ተከታታይ እርምጃ ያለማቋረጥ በመውሰድ እስረኞች ከበሽታው የሚጠበቁበትና በሕይወት የመኖር መብታቸው የሚከበርበትን መንገድ ማመቻቸት ይጠበቅበታል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ‹‹መንግስት ብዙ አበረታች እርምጃዎች የወሰደ እና ብዙ እስረኞች የተለቀቁ ቢሆንም፤ እስር ቤቶች አሁንም በእስረኞች የተጨናነቁ ስለሆነ ተጨማሪ እስረኞችን እንደአግባብነቱ በምሕረት ወይም በዋስትና በመልቀቅ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዲሁም የዋስትና መብትን በተፋጠነ መንገድ ማረጋጥ ይሻል›› ብለዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም በአሁኑ ወቅት በሁሉም ክልሎች በኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች አማካኝነት ተመሳሳይ ፈጣን ክትትል እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተቋማቸውን ሁኔታ በዚህ ፈጣን ክትትል ሪፖርት ከተለዩት ሁኔታዎች አንጻር በመገምገም፣ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋት እና አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የማስተካከያ እርምጃዎች በመውሰድ በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች በተሟላ መልኩ እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top