Connect with us

በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 81 ደረሰ

በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 81 ደረሰ
Photo: Facebook

ዜና

በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 81 ደረሰ

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ ተጨማሪ 3 ሰዎች ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸው ተገለፀ። አጠቃላይ በቫይረሱ ለህልፈተ ህይወት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 81 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 4 ሺህ 675 ሰዎች መካከል 141 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 81 ወንድ እና 60 ሴቶች ሲሆኑ ሁለቱ የውጭ አገር ዜጎች ናቸው። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከ2-87 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆኑን አመልክተዋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው 113 ከአዲስ አበባ ከተማ፣1 ከድሬደዋ ከተማ፣ 15 ኦሮሚያ፣ 3 ከጋምቤላ፣1 ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ፣ 2 ከሶማሊ፣ 6 ከሐረሪ ክልል መሆኑንም ጠቁመዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 58 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን አስታውቀው፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1544 መድረሱንም አመልክተዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 መሆኑን ጠቁመው ፥ ከእነዚህም ውስጥ 3548 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ መሆናቸውን፤ 30 ሰዎች በጽኑ ህክምና ክፍል እንደሚገኝ አስታውቀዋል። እስካሁን ለ232 ሺህ 050 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መሠራቱንም ገልፀዋል።

በቫይረሱ በአጠቃላይ 81 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ ሁለት የውጭ አገር ሰዎች ደግሞ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ አይዘነጋም።

አዲስ ዘመን ሰኔ 19/2012

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top