Connect with us

የቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት፤ የኖኅ መርከብ ወይስ የጥፋት ውሃ?

የቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት፤ የኖኅ መርከብ ወይስ የጥፋት ውሃ?
Photo: Social Media

ትንታኔ

የቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት፤ የኖኅ መርከብ ወይስ የጥፋት ውሃ?

የቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት፤  የኖኅ መርከብ ወይስ የጥፋት ውሃ?
በአምኃየስ ታደሰ | amhayest@gmail.com

ከቢል እና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን የፋይናንስ ተጠቃሚዎች መካከል የኮሮና ቫይረስን ፓተንት የያዘው ፐርብራይት ኢንስቲትዩት አንዱ በመሆኑ ቢል ጌትስ “መላው የምድራችን ነዋሪ የኮቪድ 19 ክትባትን መውሰዱ የግድ ነው” ቢል አይፈረድበትም፡፡ ምክንያቱም ጌትስ በፋውንዴሽኑ አማካይነት ባለፉት 1ዐ ዓመታት ለክትባት ምርምር ያወጣውን የ1ዐ ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ለማስመለስ ከ7.8 ቢሊዮን ከሚልቀው የምድራችን ነዋሪ ሰውነት የተሻለ የገበያ ቦታ እና ከኮቪድ 19 የተሻለ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ስለማያገኝ ነው፡፡

እንዲያም ሆኖ ከኮሮና ቫይረስ እንዲውል እየተሞከረ የሚገኘው ክትባት ተፈቅዶ ለሰዎች መሰጠት ከመጀመሩ በፊት በተጠቃሚዎች ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ተጠያቂነት ነፃ መሆኑን በመንግስታት እንዲረጋገጥ እንደሚፈልግ ቢል ጌትስ ገልጿል፡፡ በክትባቶች የሚደርሱ ጉዳቶችን በማጋለጥ እና ለተጐጂዎች በመከራከር የሚታወቁት የኘሬዝዳንት ኬኔዲ የወንድም ልጅ የሆኑት ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ የሚስጠነቅቁት በመግደል አቅሙ ከመደበኛው ጉንፋን ጋር ተቀራራቢ መሆኑ እያደር ለታወቀው የኤስሲ-2 ቫይረስ በእንስሳት ሞዴሎች ላይ ሳይሞከር በጥድፊያ የሚዘጋጅ ማንኛውም ክትባት አደጋው የገዘፈ መሆኑን ነው፡፡

ምክንያቱም በ1994 ዓ. ም. በቻይና ተከስቶ ለነበረው የሳርስ ኮሮና ቫይረስ ምላሽ ክትባት ሙከራ ሲደረግ በእንስሳት ላይ ያልተጠበቀ አስደንጋጭ ውጤት በመመዝገቡ ነው፡፡ በወቅቱ ለቫይረሱ መከላከያ በእጩነት የቀረቡት አራት ክትባቶች በእንስሳቱ ላይ ሲሞከሩ ከመነሻው አበረታች ምላሽ መስጠቱን አመላክተው ነበር፡፡ ነገር ግን እንስሳቱ ለትክክለኛው ቫይረስ ሲጋለጡ ከበሽታ መከላከል ስርአታቸው የገነነ ምላሽ እና ብግነት የተነሳ በገጠማቸው የሳንባ ፅኑ ሕመም ምክንያት ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም በ196ዐዎቹ ተሞክሮ ስኬታማ ያልሆነው የአርኤስቪ ክትባት ባስከተለው ከተገቢው በላይ የሆነ የፀረ እንግዳ አካላት እና የበሽታ መከላከል አፀፋ የተነሳ በጥናቱ የተካተቱት ሕፃናት ይጠብቃቸዋል በተባለው ክትባት ሕይወት ተቀጥፏል፡፡

ክትባት የዓለማችንን የሕዝብ ቁጥር ከ1ዐ በመቶ እስከ 15 በመቶ እንዲቀንስ አስተዋጽኦ ማድረጉን በቴድ ቶክ መድረክ የገለጸው ቢል ጌትስ ቀደም ሲል ኒው ዮርክ ውስጥ ከዋረን ቡፌት፣ ዴቪድ ሮክፌለር፣ ኤሊ ብሮድ፣ ጆርጅ ሶሮስ፣ ቴድ ተርነር፣ ኦኘራ ዊንፍሬ፣ ማይክል ብሉምበርግ እና ሌሎች ቢሊየነሮች ጋር በመሆን ከአገራት መንግስታት እውቅና ውጪ የዓለምን ሕዝብ ለመቀነስ ለመቀነስ የደረሱበትን ስምምነት እውን ለማድረግ የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ቡራኬ ከተቸረገው ወረርሽን የተሻለ አጋጣሚ አይታሰብም፡፡

ክስተቱን ወርቃማ የሚያደርገው ደግሞ በቅርቡ ግላስኮ ስሚዝ ክላይን ወይም ጂኤስኬ የተባለው የመድሃኒት አምራች ኩባንያ በሚያካሂደው ምርምር የተሳተፈ ውስጥ አዋቂ በጌትስ ፋውንዴሽን በሚደረግ ድጋፍ የሚዘጋጀው ፀረ ኤችሲጂ፣ ኦኤልኤች፣ 37 አሚኖ አሲድ እና ሲቲፒ የተባሉ ሌሎች ባእድ አካላትን የያዘው ክትባት ከተሰጧቸው 63 ሴቶች መካከል 61 ያህሉ ጨርሶ መውለድ እንዳይችሉ ለማድረግ ማስቻሉን መግለጹ ነው፡፡

የእንግሊዙ የባት ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆነው ዶ/ር አንድሪው ኘሪስተን የሚመራውና ዶ/ር ኤሪክ ሃርቪል ፣ ዶ/ር ካሮላይን ፖሊ ንዲሁም ዶ/ር ፊሊፔ ዶሆቲ እና ሌሎች ጋር በመሆን ከጌትስ በተናጠል በተበረከተላቸው ከ12 ሚሊዮን ዶላር እስከ 3ዐ ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ የተሰጣቸው ተመራማሪዎች ከጂኤስኬ ባዮሎጂካል ጋር በክትባቱ ሙከራ ላይ መጠመዳቸውን ከአስተባባሪው የዩኒቨርሲቲው ድረ ገፅ ግለ ታሪክ መገንዘብ ይቻላል፡፡

እኝሁ ተመራማሪዎች ለወንዶች ያዘጋጁት ጂኤንአርኤች የተባለ ባእድ አካል የዘር ማመንጫና የቴስቶስትሮን መጠንን እንዲቀንስ የሚያደርግ እና የስፐርም ሴሎች የኃይል አቅርቦት ማእከል የሆነውን ማይቶኮንድሪያል ዲኤንኤ ከመግደል በተጨማሪ በዝንጀሮዎች ላይ ሲሞከር ከተከተበው ወንድ ጋር ወሲብ የፈጸመች ያልተከተበች ሴት መካንነቱ እንዲተላለፍባት ማድረጉን ምስጢሩን ይፋ ባደረገው የኩባንያው ባልደረባ ተጠቅሷል፡፡

የጂኤስኤ ባዮሎጂካል በዌቭራ ቤልጅየም የሚገኝ የመድሃኒት ፋብሪካ በቀን ለ2 ሚሊዮን ሰዎች የሚሆኑ 13 የተለያዩ ክትባቶችን የማምረት አቅም ያለው የዓለማችን ግዙፉ የክትባት ማእከል ሲሆን ዶ/ር አንድሪው የሚያስተባብረው የኮቪድ-19 ክትባት በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ ላይ ለተጠቃሚ እንደሚደርስ ሲጠቁም የመድሃኒት አምራች በበኩሉ ከ1 ቢሊዮን ያላነሰ የኮኖና ቫይረስ ክትባት በማምረት ከገበያው እስከ 13 በመቶ የሚሆነውን ለመቆጣጠር ማቀዱ በሌላ ዘገባ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከ15ዐ በላይ የኮቪድ 19 እጩ ክትባቶች በተለያዩ የምርምር ሂደቶች ላይ ሲሆኑ የጌትስ ፋውንዴሽን በስሩ ባቋቋመው የትረስት ፈንድ አማካይነት ከሞላ ጐደል በሁሉም የፋርማሲ መድሃኒት አምራቾች እና የባዮ ቴክኖሎጂ ተቋማት መዋዕለ ንዋይ የሚያፈስሰው ቀድሞ የሚፈቀደውን ክትባት ለሕዝብ ቅነሳ አላማው ለማዋል እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ለአብነትም ቢል ጌትስ በቅርቡ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚበልጥ ገንዘብ ለዋየት ፋርማ፣ ሼሪንግ፣ ጊሌድ፣ ቡትስ ፋርማ፣ ዎልግሪምስ እና ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ለተባሉ የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች በክትባት ምርምር እንዲያውሉት መስጠቱ ተረጋግጧል፡፡

ከላይ ከተጠቀሰው ግላስኮ ስሚዝ ክላይን በተጨማሪም ፋይዘር፣ ፋርማሲያ፣ ብሪስቶል ሜይርስ ስኩይብ፣ ሊሊይ ባዮቴክ፡ ሜርስክ፣ ባየር፣ ባሃራትባዮ-ቴክ እና ለመሳሰሉት የፋርማሲዩቲካል ኩባንያዎች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኘው የጌትስ ፋውንዴሽን ለኮቪድ-19 ተስፋ ተጥሎበት ከነበረው ሌላው የሞደርና ክትባት ምርምር ተባባሪዎች ለሆኑት ኢኖቪዮ፣ ዊስታር፣ ቪጂኤክአይ እና ትዊስት ባዮ ሳይንስ ጭምር የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ በጐ አድራጐትንና ትርፍን አቀናጅቶ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡

በአንፃሩ በ1983 ዓ ም ከ1ዐ ሺ አሜሪካውያን አንድ የነበረው የኦቲዝም ተጠቂ አሃዝ ዛሬ ከ31 አንድ ሊደርስ የቻለው የአገሪቱ ሕፃናት ከሚወስዷቸው በድምሩ 72 ያህል ክትባቶች የተነሳ እንጂ በሌላ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ከዓለማችን ነዋሪ 1 በመቶ ያህሉ ወይም 78 ሚሊዮን የሚሆነው ተመሳሳይ የአእምሮ ዝግመት ችግር እንዳለበት እያወቅን እና ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ የኦቲዝም ሕሙማን ወይም የችግሩ ሰለባዎች አሃዝ በ15 በመቶ ሲያሻቅብ እያየን ምክንያቱ አይታወቅም የሚለውን አስተሳሰብ መቀበል ወይም ለክትባት ጉዳት ሳይንሳዊ ማስረጃ መሻት የዋሕነት ነው የሚሆነው፡፡

ምክንያቱም የክትባት ሙከራ የሚደረግባቸው ፈቃደኛ ሰዎች ለሌሎች መድሃኒቶች ምርምር እንደሚደረገው በሁለት ተከፍለው ግማሹ ትክክለኛውን ክትባት የተቀሩት ደግሞ ለመቆጣጠሪያ የሚውል ጥቅምም ሆነ ጉዳት የሌለው ንጥረ ነገር ተሰጥቷቸው በተለምዶ ከቫይረሱ የተዘጋጁት ክትባቶች በተግባር የመከላከል ብቃታቸውም ሆነ ጉዳት አለማስከተላቸው ከ1ዐ ቀን በላይ ስለማይረጋገጥ ነው፡፡

በአሜሪካው ኘሬዝዳንት ሮናልድ ሬገን በወጣ ድንጋጌ ምክንያት ለክትባቱ የሚውለውን ብቻ ሳይሆን የአሜሪካው የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ባለስልጣን የምርምሩን ትክክለኛነት ሲያረጋግጥ የሚያስፈልገውን በጀት የሚመድቡት የጥናቱ ባለቤት የሆኑት የመድሃኒት አምራቾች በመሆናቸው በሙከራ ላይ ያሉት ክትባቶች ጉዳት ቢኖራቸው እንኳን ሪፖርት አይደረገም፡፡

በዚሁ መንገድ ተፈቅዶ በዓለም የጤና ድርጅት አማካይነት የተሰራጨው የቲታነስ ክትባት በያዘው በእነ ዶ/ር አንድሪው ለኮቪድ 19 እየተሞከረ ባለው ክትባት ውስጥ ያለው ተመሳሳይ ኤችሲጂ የተሰኘ የወሊድ መቆጣጠሪያ ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁ የኬንያ ልጃገረዶችን መካን ማድረጉን የአገሪቱ ሃኪሞች ዘግይተው ማረጋገጣቸው ለዚሁ እውነታ አስረጂ ነው፡፡

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት 17ቱ የዘላቂ ልማት ግቦች 14ቱ ከክትባቱ ጋር የተያያዙ ሲሆን ለእያንዳንዱ የምድራችን ነዋሪ ዲጂታል መለያ መስጠትም የቀጣዩ 1ዐ ዓመት የዓለም አቀፍ ተቋማቱ ተቀዳሚ ተግባራት ናቸው፡፡ በአንፃሩ በቂ ምርምር ሳይደረገግባቸው እና በእንስሳት ላይ ሳይሞከሩ በጥድፊያ የሚፈቀዱት ዲጂታል ክትባቶች ከናኖ ቴክኖሎጂ፣ 5ጂ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ኤአይ፣ ብሎክ ቼን፣ ባዮሜትሪክስ፣ ወዘተ መጠቀም ጋር መቀናጀታቸው የሰውን ልጅ ከውልደት እስከ ሕልፈት ለመቆጣጠር የሚያስችል መዳረሻው እንደ ቢል ጌትስ በመሳሰሉ በሕዝብ ያልተመረጡ መሪዎችን ሳይንሳዊ የፈላጭ ቆራጭነት ስርአት ከማመቻቸት ያለፈ አይሆንም፡፡

ቶማስ ጃፈርሰን ሰዎች ምን መመገብ እንዳለባቸው እና የትኞቹን መድሃኒቶች መውሰድ እንዳለባቸው መንግስት እንዲወስን እድል ሲሰጡ ራሳቸውን በሚያሳዝን ሁኔታ ቀጥሎ የሚያገኙት በአምባ ገነኖች ስር እንዳሉት ነፍሳት ነው ማለቱ ይጠቀሳል፡፡ ስለ ኮቪድ 19 ብቸኛ እውነት ቢኖር ውሸት መሆኑን ከመገንዘብ ይልቅ መሪዎቻችን የወረርሽኝ እምቢልታ ማስተጋባቱን የፈለጉት የስልጣን ዘመንን ከማራዘም ባለፈ ታላቁ ጅማሮ ያሉትን አዲሱን የዓለማችን ስርአት ከማስፈጸም አንፃር ከሆነም ቢያንስ የክትባቱ ተጐጂ አለመሆናችንን በቅድሚያ ሊያረጋግጡልን ይገባል፡፡

በመጨረሻም ቢል ጌትስ በክትባቱ ከሚደርስ ጉዳት በኃላፊነት እንዳይጠየቅ በማመቻቸት ለዘመናዊ ባርነት የሚዳርገንን ውጥን ማክሸፍ የማንም ኃላፊነት ሳይሆን በተለይ ለቅኝ ግዛት ተንበርክከን የማናውቀው የእያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን ድርሻ ሊሆን ይገባል፡፡

በጽሁፉ ወደተገለጹት መረጃዎች የሚወስዱትን የተለያዩ ሊንኮች በመክፈት ጭምር እውነታውን ተገንዝበን ዘመቻውን ከማስቆም ይልቅ ዝምታን ከመረጥን የኋላ ኋላ የእኚሁ ጥቂት አረመኔ እንስሶች መጫወቻ መሆናችን አይቀሬ ነው፡፡ በወረርሽም ስም ሊፈጸም የታሰበውን የዘር ማጥፋት ወንጀም መቃወም ካለብን ጊዜው አሁን ብቻ ነው፡፡

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top