Connect with us

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!
Photo: Social Media

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!

#እንኳን_አደረሳችሁ_አደረሰን!!

ዕለተ እሁድ:- ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም።
በተመሳሳይ ቦታ በ375 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ በድጋሚ ለሚከሰተው ብርቅዬው #የጸሐይ_ግርዶሽ ቀን እንኳን በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን።
እርስዎና እኛ ለዚህች ታሪካዊ ቀን በመብቃታችን ዕድለኞች ነን። ፈጣሪ ይመስገን!!
***

በዛሬው ዕለት ስለሚከሰተዉ የጸሃይ ግርዶሽ እና የአይናችንን ጉዳይ 10 እዉነታዎች ዛሬም ልብ ሊሉና መልዕክቱን ለወዳጅ ዘመድ በፍጥነት ሊያካፍሉ ይገባል!

1. የጸሀይ ግርዶሽ ምንድነዉ?
✍️ጨረቃ ምድራችንን በምህዋር በምትዞርበት ግዜ አንዳንዴ በፀሀይ እና በምድር መሀል በአንፃራዊነት በቀጥታ መስመር ትሰለፋለች። በዚህ ምክንያትም ከፀሀይ ለምድር የሚደርሰውን ብርሀን ትጋርዳለች፤ ይህ የጨረቃ ጥላ ምድራችን ላይ ሲያርፍ የፀሀይ ግርዶሽ ተከሰተ ይባላል።

2. የጸሀይ ግርዶሽ ክስተት ምንድነዉ ብርቅ የሚያደርገዉ?
✍️ምክንያቱም ይህ ክስተት በተመሳሳይ ቦታ በድጋሚ የሚከሰተው በአማካይ በ375 ዓመት ውስጥ አንዴ ስለሆነ ነው።

3. የዘንድሮዉ ጸሃይ ግርዶሽ በደንብ የሚታይባቸዉ ቦታዎች (98% ጸሃይ የምትጋረድበት) ቦታዎች ?
✍️በተለይ ወለጋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አላማጣ፣ ኢንጂባራ 98% ጨለማ ሆኖ ይታያል፡፡
ነገር ግን በ አዲስ አበባ ግረዶሹ ከፊል በመሆን ከ ጠዋቱ 12፡49 እስከ ጠዋቱ 3፡15 ደቂቃ ለ 2 ሰዓታት ከ 26 ደቂቃዎች ብቻ ይቆያል።

4. ግርዶሹ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል?
✍️ለ 6 ሰዓታት ያህል። ሰኔ 14/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡45 እስከ ቀኑ 6፡33

5. ግርዶሹ የሚታይበት እና የሚያበቃበትስ ቦታ?
✍️ከማዕከላዊ አፍሪካ ከኮንጎ ይነሳል፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ታይዋን፣ ህንድና ቻይናን አቋርጦ ፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ያበቃል፡፡

6. ያለ ግርዶሽ መነጽር ብናይ አይናችን ሊጎዳ ይችላል?
✍️አብዛኛዉን ጊዜ ግርዶሽ ሲከሰት ሰዎች አይናቸዉን የሚጎዳ ስለማይመስላቸዉ ለረጅም ጊዜ ጸሃይን በሚያዩበት ጊዜ ከጸሃይ ጨረሮች መካከል አልትራቫዮሌት (UV) ጨረር ቀጥታ ሬቲና የተሰኘዉን እና ምስል የሚሰራበትን የአይን ክፍል ላይ በማረፍ ሙቀቱን ከ 4 ድጊሪ ሴንቲግሬድ በላይ በሚያሞቅበት ጊዜ ከሚከሰት የኬሚካል ጉዳት የተነሳ ያ ቦታ የማየት አቅሙን ያጣል። ይሄንንም ኤክሊፕስ ሬቲኖፓቲ (Eclipse Retinopathy) በመባል ይጠራል።

7. ግርዶሽን ያለመነጽር ከማየት ዉጪ ሌላ አይን የሚጎዳበት ሁኔታ አለ?
✍️ትክክለኛዉን መነጽር ካልሆነ እና ሌሎች የተለያየ አይነት ግልጋሎት ያላቸዉን ሌንሶች ያሉባቸዉን መነጽሮች መጠቀም በቀጥታ የቃጠሎ አደጋ ሬቲና ላይ እንዲደርስ ሊያደርግ ይችላል።

8. ለምን ያህል ጊዜ ያለመነጽር በቀጥታ ቢታይ ነዉ አይን ሊጎዳ የሚችለዉ?
✍️ቢያስ ለ 100 second (ለ አንድ መቶ ስኮንድ፣ ከአንድ ደቂቃ እስከ 2 ደቂቃ) መመልከት ጉዳቱን ሊያደርስ ይችላል። ስለዚህ በተቻለ መጠን ህጻናት ወይም ደግሞ ግንዛቤዉ የሌላቸዉ ሰዎች ለረጅም ጊዜ እንዳያዩ ማድረግ ይመከራል።

9. የአይን ህመሙ ምልክት መቼ ይታወቃል?
✍️ለጸሀይ ከተጋለጡበት ከ ጥቂት ሰዓታት ጀምሮ፡ የአይን ማቃጠል፣ የራስ ምታት፣ ብርሃን ማየት መክበድ እና የአይን መቆርቆር ሊጀምሩ ይችላሉ።

10. የአይን ህመሙ ህክምና አለዉ?
✍️አይናችን በዚህ ምክንያት ከተጎዳ የሄ ነዉ የሚባል ህክምና የለዉም፣ ነገር ግን እንደየ ጉዳቱ ከ ጥቂት ሳምንታት እስከ አንድ አመት ድረስ በመቆየት በራሱ ጊዜ ይድናል። ነገር ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ከሆነና እድሜ ልክ እይታ ሊታጣ ይችላል።

መፍትሄው፡-
ሀ. ትክክለኛ ያልሆኑ እና ጥራታቸዉ ያልተረጋገጡ መነጽሮችን መጠቀም በቀጥታ ያልተናነሰ ወይም ደግሞ የባሰ ሊጎዳን ስለሚችል፣ ግርዶሹን በተቻለ መጠን ላለማየት መሞከር።

ለ. ማየት ግዴታ ከሆነ ፒን ሆል ካሜራ ( Pin Hole Camera) ከካርቶን፣ ከፊል ብርሃን ከሚያሳልፍ ወረቀት እና አሉሚኒዬም ፎይል በመስራት መመልከቱ ይመከራል።

#Africare

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top