Connect with us

“ልጄን በቀለሟ የሚያገል ህግን እልደግፍም” አንጀሊና

"ልጄን በቀለሟ የሚያገል ህግን እልደግፍም" አንጀሊና
Photo: Social Media

ጥበብና ባህል

“ልጄን በቀለሟ የሚያገል ህግን እልደግፍም” አንጀሊና

“ልጄን በቀለሟ የሚያገል ህግን እልደግፍም” አንጀሊና

(ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)
እውቅ አሜሪካዊት የሲኒማ ተዋኒት፣ዳይሬክተር እና የስብአዊ አገልግሎት አምባሳደር አንጀሊና ጁሊይ ለእርሷ እና መሰል ነጮች ብቻ የቆመ፣በተቃራኒው የእርሷን ትውልደ ኢትዬጵያዊት ሴት ልጅን ሆነ ሌሎችን በቆዳቸው ቀለም መጥቆር ብቻ የማያከብር ህግን እንደማትደግፍ ተናገረች።

የአርባ አምስት አመቷ የኦስካር ተሸላሚዋ ፣አንጀሊና ሃርፐር ባዛር ዩኬ ከተባለ መጽሔት ጋር ባለፈው አርብ እለት ባደረገችው ቃል ልምልልስ”ለእኔ ጥበቃ የሚያደርግ ፣ ነገር ግን ለሴት ልጄ(ዘሃራ) ፣ለሌሎች ወንዶች እና ሴቶች በቆዳቸው ቀለም መጥቆር ብቻ የሚያገል ስርዓትን(ሲስተም)አልታገሰውም” በማለት ዘረኝነት ከስድስት ወሯ ጀምሮ ያሳደገቻት የትውልደ ኢትዮጵያዉቷ፣ ዘሀራን እጣ ፈንታን ጭምር ሊያጠቃ እንደሚችል አቋሟን ገልጻለች ።

ለዘረኝነት ሰለባዎች እና ተጠቂዎች ከንፈር ከመምጠጥ እና ሀዘንን ከመግለጽ ባሻገር ፣ፖሊሲዎች እና ህጎች መቀየር እንዳለባቸው የተናገረችው አንጀሊና በአሜሪካው ሚኒሶታ ግዛት በጥቁር አሜሪካዊው ፣ጆርጅ ፍሎይድ ላይ ባለፈው ግንቦት 25/2020 እኤአ በነጭ ዘረኞች ፖሊሶች በግፍ መገደል ያስቆጣት መሆኑን የገለጸች ሲሆን “በአሜሪካ የተጀመረው የተጠያቂነት እንቅስቃሴ ጥሩ ጅማሮ ነው፣እንቅስቃሴው በማህበረሰቡ ውስጥ፣በትምህርት ቤት እና በፖለቲካው ውስጥ ሊሰርጽ ይገባል”ስትል አቋሟን ገልጻለች።

የጥቁሮች መብት ያገባናል/ብላክ ላይፍ ማተርስ/ የሚለው አለማቀፋዊ እንቅስቃሴ አውቆ የተኛው የአለም ህዝብን የቀስቀሰ ታላቅ ለውጥ መሆኑን የጠቆመችው አንጀሊና”በገዛ አገራቸው እንደ ባይተዋር የተቆጠሩ ጥቁር አሜሪካኖች ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል፣ተቋማቱም ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋቸዋል” ስትል ጥሪ አቅርባለች።

ከቀድሞው ባላቤቷ ከታዋቂው የሲኒማ ተዋናይ ብራድ ፔቲት ከወለዷቸው ሶስት ልጆች በተጨማሪ የአስራ አምስት አመቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዘሃራን ጨምሮ ስድስት ልጆች አፍርተዋል።

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top