Connect with us

ይህ ትውልድ ቁጭቱን መቋጨት የሚጀምርበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ቀናት ተቆርጠውለታል

"ይህ ትውልድ ቁጭቱን መቋጨት የሚጀምርበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ቀናት ተቆርጠውለታል"

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ይህ ትውልድ ቁጭቱን መቋጨት የሚጀምርበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ቀናት ተቆርጠውለታል

“ይህ ትውልድ ቁጭቱን መቋጨት የሚጀምርበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ቀናት ተቆርጠውለታል”

ዶ/ር አብርሃም በላይ
የኢንኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

..እለተ እሁድ ሰኔ 7/2012ዓ.ም የክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች ጋር የህዝባዊ ቁጭታችን መቋጫ ምን እንደደረሰ ለመጎብኘት ቤንሻንጉል ጉባ ከትተናል::የህዳሴ ግድባችንና ወቅታዊ ሁኔታውን ለመገምገም እና ያለበትን ደረጃ በቦታው ተገኝቶ ለማየት::

የኢትዮጵያ ህዝቦች ባለፋት 9 ዓመታት ለመንግስት ከሰጡት ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነትና ተልእኮዎች መካከል የትውልድ ኣሻራ የሆነውን የህዳሴ ግድባችንን ዳር የማድረስ ጉዳይ ኣንድ መሆኑ ይታወቃል::

በብዙ ፈተናዎች የሚያልፈው ይህ ፕሮጀክታችን ውሃ መያዝ የሚጀምርበት የግዜ ሰሌዳ በቀናት ውስጥ የሚቆጠሩት ሆነዋል::

 

ርእሳነ መስተዳደሮቹ ወደየ ክልሎቻቸው ሲመለሱ ኣጥጋቢ ሪፖርት ይዘው የተመለሱ ሲሆን በዚህም ከጅምሩ ኣንሰቶ የላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ የታየበት ይህ ፕሮጀክታችን ያለበትን የእድገት ደረጃ ዜና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለዘመናት ለተጠሙ ጆሮዎች በደስታ ያደርሳሉ::

"ይህ ትውልድ ቁጭቱን መቋጨት የሚጀምርበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ቀናት ተቆርጠውለታል"

..እለተ እሁድ ሰኔ 7/2012ዓ.ም የክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች ጋር የህዝባዊ ቁጭታችን መቋጫ ምን እንደደረሰ ለመጎብኘት ቤንሻንጉል ጉባ ከትተናል::የህዳሴ ግድባችንና ወቅታዊ ሁኔታውን ለመገምገም እና ያለበትን ደረጃ በቦታው ተገኝቶ ለማየት::

አሁንም መልእክታችንና መርሆዎቻችን ግልፅ ናቸው::*

1. የናይል ተፋሰስ ላይ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥና የሚያበረታታ ነባራዊ የመሬት ሐቅና ምልክት ማሳረፍ::

2. በመልማት ፍላጉቶቻችን ዕቅዶቻችን ውስጥ የታችኛው ተፋሰስ ሃገራትን

ድህነትና ጥቅም ግንዛቤ ውስጥ በመክተት በተጠኑ ዘላቂ የልማት ፕሮግራሞቻችን ያለማቀፍ ሕግጋቶች ተገዥነታችንን በተግባር ማስመስከር::

3. ፕሮጀክታችንን በጥራት በተያዘለት ግዜ ገደብ በማጠናቀቅ የሀይል ፍላጎት ኣቅርቦታችንን ከማረጋገጥ ባሻገር የኣከባቢ ትስስር ኣበርክቶ ጅማሮዎቻችንን ማጎልበት::

ጆሮ የማንሰጣቸው የትንኮሳ ድምፆች:

1. የኢትዮጵያ ህዝቦች ዛሬን በትላንት ላይ ብቻ ቁሞ ኣይመዝንቱም::የሕግና የርትእ መደገፍያ ጠጠር የማይገኝላቸውን “የታሪካዊ ባለቤትነት”ትርክቶችንም የሚሰሙበት ጆሮ የላቸውም::

2. ኣስተዋይ ህዝባችንና ሃላፊነት የሚሰማው መንግስታችን ዘመኑ ለሚጠይቀው ስልጡን ምክንያታዊ ውይይትና ተገቢ ድርድር ቅድሚያ ይሰጣሉ ከዚህ በተቃራኒ ጫና ዛቻና ቀቢፀ ተስፉ የማንጃበብ ሙከራዎችን ግን በንቃት ይከታተላል:: ኣሁንም የዚህ ታላቅ ህዝብ ታሪካዊ ምክር ትብብርና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ይረጋገጥ ብቻ ነው::

ከዚህ ውጭ ላሉ ሙከራዎች የታሪክ መዛግብት በድጋሚ እንዲመረመሩ እያበረታታ ያለ ፋታ የወደፊት ግስጋሴውን ይቀጥላል::

እነዚህ የህዝብ ወኪሎች በተጨማሪም የኣከባቢ ሚዛን ጥበቃን የሚያበለፅጉ የኣረንጋዴ ልማት ስራዎችን በመቀጠልም ዛሬም በህዳሴ ግድብ በኣካል ተገኝተው ኣረንጓዴ ኣሻራቸውን በስማቸው እና በሚወክሉት ህዝብ ስም በክብር ኣሳርፈዋል::

ውድ የኢትዮጵያ ህዝቦች:

እንደተለመደው ልዩነቶቻችንን ለጊዜው ወደ ጎን እንድንተው በኣንድ የሚያስተሳስረንን የትውልዱ የቁጭት ኣጀንዳችንን የህዳሴው ግድብ የማጠናቀቅያ ምዕራፍ ስራዎችን ኣሁንም በንቃት ተከታተሉ:: ያልተቆጠበ ድጋፍና ተሳትፎኣቹሁንም በቀጣይነት ከማረጋገጥ ወደ ኃላ እንዳትሉ።

ልኣላውነታችንን በሙልእነት ለተቀረው ኣለም የምናንፀባርቅበት የህዳሴው ፕሮጀክታችንንም በሉኣላዊ ግዛታችን ያለ ማንም ፈቃድና ከልካይ በራሳችን ገንዘብ እውቀትና ጉልበት በመገንባት ዘመናዊ የጀግንነት ታሪክን በደማቁ ለመፃፍ ክንዳችንን እናፅና::

ድል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለሚያስተጋባ ኢትዮጵያዊያን ድምፆች!!

ፈጣሪ ሀገራችንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top