Connect with us

ብልፅግና እና ህወሓትን የሚሸመግል ቡድን ወደመቀለ ይጓዛል

ብልፅግና እና ህወሓትን የሚሸመግል ቡድን ወደመቀለ ይጓዛል
Photo: Facebook

ዜና

ብልፅግና እና ህወሓትን የሚሸመግል ቡድን ወደመቀለ ይጓዛል

የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ጉባኤ ልዑክ በነገው ዕለት ወደ ትግራይ በመሔድ ከክልሉ መንግስትና ሌሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር ይነጋገራል ተብሏል።

52 አባላት ያሉት የሀገር ሽማግሌ ቡድን ወደ መቀለ የሚሔዱት በራሳቸው ተነሳሽነት ሲሆን የሀይማኖት መሪዎች፤ ታዋቂ ሰዎች፤ ምሁራን የተካተቱበት ነው።

በሽምግልና ቡድን ውስጥ ከተካተቱት መካከል ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ ቀዳዊ ፤ ብፁዕ ካርዲናል ብርሐነእየሱስ፤ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ፤ ፓስተር ፃዲቁ አብዶ፤ ፓስተር ታደሰ አዱኛ፤ ዶክተር ዮናስ ይገዙ ፤ ዶክተር እያሱ ኤሊያስ እንዲሁም ከታዋቂ ሰዎች ደግሞ አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ 52 ሰዎች ይገኙበታል።

የጉዞው ዋና አላማም ባለፉት ሁለት አመታት በትግራይ ክልል መንግስት እና በፌዴራል መንግስት መካከል እየተፈጠረ ያለው ልዩነት በህዝቦች አንድነት ላይ እየተፈጠረ ያለው መቃቃር ለማስቀረትና ለማጥበብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው።

ቡድኑ በትግራይ በሚኖረው ቆይታ ከክልሉ መሪዎች ፤ የሀገር ሽማግሌዎችና ተወካዮች ጋር እርቅና መግባባት እንዲፈጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራል መባሉን የአውሎ ሚድያ ዘገባ ያሳያል።

በተለይም በፖለቲካ ሀይሎች መካከል ያለው አለመግባባት በህዝቦች ነባርና የቆየ ግንኙነት ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና እየሰፋ በመሆኑ የትግራይ ክልል መንግስትና የፌዴራል መንግስት ወደ መግባባት የሚመጡበትን መንገድ ላይ በዋናነት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል ።

ቀደም ሲል በኢህአዴግነት የሚታወቁትና ከውህደት በኃላ በተፈጠረ ልዩነት በዋንኛነት በብልፅግ እና በህወሓት መካከል ያለው የፓለቲካ ልዩነት ከጊዜ ወደጊዜ እየተካረረ ወደግጭት የማምራት አዝማሚያ መያዙ ሠላም ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ማሳሰቡ አይዘነጋም።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top