Connect with us

ቫይረስ ፈርተን በቁም ከመቀበር

ቫይረስ ፈርተን በቁም ከመቀበር
The donkey and the well (Personal research)

ጥበብና ባህል

ቫይረስ ፈርተን በቁም ከመቀበር

ቫይረስ ፈርተን በቁም ከመቀበር
አምኃየስ ታደሰ
amhayest@gmail.com

“አባባ እንዳንተ ብርቱ ለመሆን የምችለው እንዴት ነው?” የሚል ጥያቄ ለአያቱ ያቀረበው ውርንጭላ ከአረጋዊው አህያ የተሰጠው ምላሽ “መጠንከርም ሆነ ማደግ የሚቻለው እያራገፉ ወደ ላይ መውጣት ሲቻል ነው” የሚል ነበርና በአባባሉ ግራ መጋባቱን ገለፀ፡፡ “እንዳንተ ልጅ እያለሁ በአንዱ ዕለት የዚህ የከብቶች ማጐሪያ መዝጊያ በአጋጣሚ ክፍቱን ተረስቶ አገኘሁ፡፡ ከበረቱ አምልጩ በመውጣት በመስኩ ላይ በነፃነት መቦረቅ ጀመርኩ፡፡ የተራሮቹን ግዝፈት እና መጨረሻ የሌለውን የሰማይ ውበት እያደነቅኩ እግሬ በመራኝ አቅጣጫ ስጓዝ ድንገት በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ወደቅኩ፡፡

“መውጣት በማልችልበት ሁኔታ ራሴን መቀመቅ ውስጥ በማግኘቴ ሞቴን በትዕግስት ከመጠበቅ በስተቀር ምርጫ እንደሌለኝ ተገነዘብኩ፡፡ በቀቢፀ-ተስፋ የሚሆነውን ስጠባበቅ ድምፅ መስማቴን ተከትሎ አንድ ገበሬ ወደ ጉድጓዱ አፍ ተጠግቶ ቁልቁል ወደ እኔ እየተመለከተ መሆኑን ተገነዘብኩ፡፡ ሰውዬው ወዲያውኑ ተመልሶ ከሄደ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ተሽከርካሪዎች ተከታትለው ወደ ጉድጓዱ ተጠግተው ሲቆሙ ተሰማኝ፡፡

“በርግጥም ቀደም ሲል ብቻውን መጥቶ የነበረው ሰውዬ ሌሎችን አስከትሎ በመምጣቱ ተጋግዘው ሊያወጡኝ እንደሆነ በማሰብ ሃሴት ባደርግም ገበሬው ለጓደኞቹ‘ አማራጭ መንገድ የለም፤ አህያዋም የመውጣት ዕድል የላትም፤ በሉ ጉድጓዱን እንሙላ’ ሲላቸው ከተሽከርካሪዎቻቸው ዶማና አካፋ በማውረድ የዙርያውን አፈር እየቆፈሩ ወደ ጉድጓዱ መመለስ ጀመሩ፡፡ ከላይ የሚወረወረው አፈር ሸኮናዬን ቀስ በቀስም ቁርጭምጭሚቴን መሸፈን ሲጀምር በቁሜ ተቀብሬ መሞቻዬ መድረሱን ተረዳሁ፡፡


“ወዲያውኑ ሕይወቴን ለማትረፍ ያለኝን አማራጭ ሁሉ መጠቀም እንዳለብኝ ታሰበኝ፡፡ እናም ጀርባዬ ላይ የሚያርፈውን ኮረት አራግፌ እላዩ ላይ መውጣት ጀመርኩ፡፡ ሰዎቹ ወደ ጉድጓዱ ኮረቱን ሲመልሱ እኔም ከጀርባዬ ላይ ሳራግፍ እና አፈሩን እየረገጥኩ ወደ ላይ መውጣቴን ቀጥዬ በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ በመውጣት ተመልሼ መሬት ለመርገጥ ቻልኩ እልሃለሁ፡፡

“በርግጥም በወደቅኩበት ጉድጓድ ውስጥ ቀብሮ እዚያው ሊያስቀረኝ የነበረውን አፈር አሽቀንጥሬ እየጣልኩ እላዩ ላይ በመውጣቴ እነሆ በሕይወት ልቆይ በቃሁ፡፡ አስታውስ፤ ብርቱ ለመሆን ወይም የምታልመውን ዕውን ለማድረግ የሚጫንብህን እና ቁልቁል ሊያስቀርህ የሚሞክረውን ሁሉ እያራገፍክ ወደ ላይ ከመውጣት በስተቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለህ ተረዳ፡፡”

ለመሆኑ እኛስ?
ሰውን ከእንስሳት ከሚለዩት ባሕርያት አንዱ በተለይ ኘሪፍሮንታል ኮቴክስት (Prefrontal Cortex) ወይም ፒኤፍሲየሚባለው የላይኛውን ጭንቅላቱን የያዘው የአንጐሉ ክፍል በአንፃራዊነት መግዘፉ ሲሆን ይኽም ኃሳቡንና ስሜቱን አቀናጅቶ ውስብስብ የሆኑ ደንቃራዎቹን ለመፍታት አርቆ እንዲያስብ፣ እንዲያመዛዝን እና እንዲወስን የሚያስችሉን ተግባራት የሚያከናውንበት የሰውነቱ ክፍል ነው፡፡

እንዲያም ሆኖ ሰብአዊ ፍጡር ተብሎ ከሚታወቀው ምን ያህሉ አእምሮውን እንደሚጠቀም በርግጠኝነት መናገር ስለማይቻል ይሆናል ናታን ፍሬዘር “በዓለማችን ላይ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፤ እነሱም መንግስት እንደሚጨነቅላቸው የሚያስቡ እና ራሳቸው የሚያስቡ ናቸው” ሊል የቻለው፡፡

ከዚህም አንፃር ጭንቅላታችንን መጠቀም ትተን ሌሎች እንዲያስቡልን የምንጠብቅ ከሆነ አሁን በቤታችን ከምንገኝበት የቁም እስር እንደ አህያዋ በቁም ወደ መቀበር እያቀናን መሆኑን ልንገነዘብ የሚገባው አሁን ይመስለኛል፡፡ በተለይ ምንም አይነት ሳይንሳዊ መሠረት በሌለው በምናባዊ ቫይረስ እና ሰው ሰራሽ ወረርሽኝ ሳቢያ በገዛ ቤታችን ግዞተኛ የሆንነው እኛ ከአህያው ተሽለን ለመገኘታችን ምን ያህል እርግጠኞች ነን?

በተለይም ራሱን የዓለማችን ንጉሰ ነገስት ያደረገው ቢል ጌትስ የመገናኛ ብዙሃንን ተጠቅሞ እና በተለይ የድሆች አገራት መሪዎችን ደልሎ እና አታልሎ ወረርሽኝ ፈርተን መስራት አቁመን ገቢያችን ቀስ በቀስ እየተሟጠጠ ሙሉ በሙሉ ተመጽዋች ስንሆን ጠብቆ የሚሯሯጥለት የዲጂታል ክትባት ሰለባ ሳያደርገን ካሸለብንበት እንንቃ!

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top