Connect with us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንትና ሠራተኞች ክብር ይገባቸዋል …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንትና ሠራተኞች ክብር ይገባቸዋል
Photo: Social media

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንትና ሠራተኞች ክብር ይገባቸዋል …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንትና ሠራተኞች ክብር ይገባቸዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአየር መንገዱን ስምና ክብር መሰከሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች በመለሱበት ስብሰባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ እጅግ የሚመሰገን መኾኑን መስክርዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በግብታዊነት አየር መንገዱ በረራውን ያቁም በሚል ሲነሳ የነበረው ወቀሳና ተቃውሞ ያልተጠናና ከውጤቱ ተቃራኒ የነበረ ፍላጎት መሆኑን አሳይተዋል፡፡ የአየር መንገዱ ማኔጅመንትና ሰራተኞችም ክብር ይገባቸዋል ሲሉ አክብሮታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአየር መንገዱ ስም በሀገር ደረጃ ያኮራቸው መሆኑንና በሀገራት መሪዎች ጭምር የተመሰገኑበት ስለመሆኑ መስክረዋል፡፡ ዶክተር አብይ አየር መንገዱ የሰራው ስራ ራሱንና ስሙን አስጠብቆ ከመቀጠል ባለፈ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የተጫወተውን አስተዋጽኦ ለህዝብ እንደራሴዎቹ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጥንቃቄ የተጓዘበት አግባብና መንገድም ውጤቱ ስኬታማ ከመባል ባለፈ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ ያመጣ ድህረ ኮሮና ተወዳዳሪነቱን በክብር አስጠብቆ ማስቀጠል የሚችልበትን ሁኔታ የፈጠረ እንደሆነ ነው የተጋነገሩት፡፡

ባለፉት ተከታታይ ወራት በኢትዮጵያ ታሪክ ለተከታታይ ስምንት አስርት ዓመታት የዓለም ክብርና ደረጃውን ጠብቆ የቀጠለው ብቸኛው የሀገሪቱ ተቋም ብዙ ወቀሳዎች ሲቀርቡበት ቆይተዋል፡፡ ኮሮናን አስመልክቶ የኦርፐሬሽን ስራው በስሜታዊነት ይቁም በሚሉ ወገኖችና እስከአሁንም የአየር መንገዱን ስምና ክብር አስጠብቆ በቀጠለው የአየር መንገዱ አመራር መካከል ሰፊ የአስተሳሰብ ልዮነቶች ታይተዋል፡፡ ያም ሆኖ አየር መንገዱ ይሆናል ያለው ግብ በስኬት እየቀጠለ ሲሆን ያደርሳል የተባለው ጉዳትና ጥፋት ግን ከስጋት ያለፈ መሆን አልቻለም፡፡

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top