Connect with us

የጭነት አገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር በዕጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

የአየር መንገዱ የጭነት አገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር በዕጥፍ መጨመሩ ተገለጸ
Photo: DireTube

ኢኮኖሚ

የጭነት አገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር በዕጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

የአየር መንገዱ ተሳፋሪዎች ቁጥር በ80 በመቶ ቢቀንስም የጭነት አገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር በዕጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የላቲን አሜሪካ ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ግሩም አበበ እንዳሉት የአውሮፕላን ተሳፋሪዎች ቁጥር በ80 ከመቶ ቢቀንስም ፣ የጭነት ፍላጎት በእጥፍ ጨምሯል በመሆኑም 25ቱ አውሮፕላኖች የጭነት አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጎ እየተሰራ ነው።

የኢትዮዽያ አየር መንገድ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አስፈላጊ የተባሉ የህክምና ቁሶችን ወደ ላቲን አሜሪካ ለማድረስ ተመራጭ አገልግሎት ሰጪ ሆኗል ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።

አቶ ግሩም አበበ እንደተናገሩት ከሆነ በክፉም ሆነ በበጎ ወቅቶች ሰዎች የእኛን እገዛ ሲፈልጉ መርዳት እንዳለብን እንገነዘባለን አየር መንገዱ ሁሌም ህዝብን በማገልገል ላይ ነው ብለዋል።

የብራዚል መንግሥት አዲስ አበባን እንደ መሸጋገሪያ ማዕከል አድርጎ ከቻይና የተገዙና የተለገሱ የህክምና መሳሪያዎችን ለመውሰድ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

የኢትዮዽያ አየር መንገድ 360 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት ባስገነባው ተርሚናል በመጠቀም የህክምና መሳሪያዎቹን ከብራዚል በተጨማሪ ወደ ቺሊ፣ ኮሎምቢያና ኢኩዋዶር እያደረሰ ሲሆን ወደ አርጀንቲናና ፔሩ ለማቅረብም እቅድ እንዳለው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።

አንድ መቶ ሰላሳ መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮዽያ አየር መንገድ የውጭ ምንዛሪ በማምጣት ለአገሪቱ ምጣኔ ሃብት የበኩሉን ድርሻ እያበረከተ እንደሆነ ኤዜአ ፋይናንሺያል ታይምስን ጠቅሶ ዘግቧል።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top