Connect with us

የብልጽግና ፓርቲ በመቀሌ ከተማ ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ አወገዘ

የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ፓርቲ ጽ/ቤት በመቀሌ ከተማ ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ አወገዘ

ዜና

የብልጽግና ፓርቲ በመቀሌ ከተማ ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ አወገዘ

የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ፓርቲ ጽ/ቤት በመቀሌ ከተማ ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ አወገዘ

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የክልሉ ፖሊስ በትናንትናው እለት በመቀሌ ከተማ የወሰደው እርምጃ አወገዘ፡፡ የክልሉ ፖሊስ በከተማዋ 05 በሚባለው አካባቢ ተሰብስበው መጠጥ ሲጠጡ ነበር ያላቸውን ወጣቶች ለመበተን በወሰደው እርምጃ 1 ወጣት በፖሊስ ጥይት ተመትቶ ሲሞት ሌሎች ሶስት ወጣቶች ቆስለዋል የንብረት ውድመትም ተከስቷል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የትግራይ ቅርንጫፍ ሀላፊ አቶ ነቢዩ ስሁል የፖሊስር እርምጃ “በጭካኔ የተሞላ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡

አክለውም ግድያውና አጠቃላይ ጥቃቱ በትግራይ ክልል የሚገኘው የፀጥታ ሃይል አመራር ላይ በሰፊውና በተደጋጋሚ ሲንፀባረቁ የቆዩ ጉልህ የብቃት ማነስ፣ የስልጠና/የዶክትሪኔሽ መዛባትና የኢ-ህዝባዊነት ባህሪ ማረጋገጫ ሲሆን አጠቃላይ ችግሩም ክልሉን እስካሁን እያስተዳደረ ያለውን መንግስትና ስርዓት መሰረታዊ የኢ-ህዝባዊነትና ለመንግስታዊ ሃላፊነት ብቁ ያለመሆን ችግሮች ነፀብራቅ ነው” ብለው ይህን የፈጸሙ የጸጥታ ሀይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ተግባሩን የፈጸውም አባል በቁጥጥር ስር መዋሉን ማሳውቁን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል፡፡

(አዲስ ልሳን ጋዜጣ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top