Connect with us

ውሃና ፍሳሽ 362 ሚልየን ብር ደንበኞቼ አልከፈሉኝም አለ

ውሃና ፍሳሽ 362 ሚልየን ብር ደንበኞቼ አልከፈሉኝም አለ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

ውሃና ፍሳሽ 362 ሚልየን ብር ደንበኞቼ አልከፈሉኝም አለ

የአገልግሎት ክፍያ በአግባቡ አለመከፈሉ ህልውናዬን አየተፈታተነው ነው አለ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ የበኩሉን እየተወጣ ቢገኝም ገቢን መሰብሰብ አለመቻሉ በስራው ላይ እንቅፋት ሆኖብኛል ነው ያለው።

በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ሰርካለም ጌታቸው እንዳስታወቁት፥ የመጋቢት ወር የአገልግሎት ክፍያ መከፈል ከነበረበት ክፍያ 28 በመቶ ብቻ ነው የተፈጸመው።

ዳይሬክተሯ ከግለሰቦች አንስቶ የፌደራል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት፣ ሆቴሎች እና የግል ድርጅቶች ናቸው ክፍያቸውን ያልከፈሉት ብለዋል።

በመግለጫው እንደተነሳው በአንድ በኩል በኮሮና ምክንያት ከፍተኛ የስራ ጫና ውስጥ የሚገኝው ተቋሙ በክፍያ ምክንያት ለሰራተኞቹ ደሞዝ ለመክፈል መቸገሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንዳያስተጓጉለው ስጋት አለኝ ብሏል።

ተቋሙ 362 ሚሊየን ብር በላይ ያልተከፈለ ውዝፍ አለኝም ብሏል።

በተለይም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የውሃ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ያሉት ዳይሬክተሯ፥ በከተማው በውሃ ፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ ነውም ብለዋል።

ባለስልጣኑ የውሃ አግልግሎት ክፍያቸውን በአግባቡ በማይከፍሉ አካላት ላይ አገልግሎት በማቋረጥ በህግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። (ፋና)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top