Connect with us

በቻይና ጂያንግሱ ግዛት የምትገኘው ኩንሻን ከተማ ለድሬዳዋ ከተማ …

በቻይና ጂያንግሱ ግዛት የምትገኘው ኩንሻን ከተማ ለድሬዳዋ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያግዙ የሕክምና መሣሪያዎችን አበርክታለች
Photo: Facebook

ዜና

በቻይና ጂያንግሱ ግዛት የምትገኘው ኩንሻን ከተማ ለድሬዳዋ ከተማ …

ድሬዳዋ ከተማ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያግዙ የሕክምና መሣሪያዎችን ከቻይናዋ የኩንሻን ከተማ በድጋፍ አገኘች

በቻይና ጂያንግሱ ግዛት የምትገኘው ኩንሻን ከተማ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያግዙ የሕክምና መሣሪያዎችን ለድሬዳዋ ከተማ አበርክታለች።

የሕክምና መሣሪያዎቹ በአጠቃላይ 70 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ አምስት አጋዥ መተንፈሻዎች (ቬንትሌተሮች)፣ 50 ሺህ ለአንድ ጊዜ የሚያገለግሉ ጭምብሎች፣ 5 ሺህ 120 KN95 ጭምብሎች እና 600 የሐኪሞች መከላከያ ልብሶች እንደሆኑ ተነግሯል።

የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አህመድ ቡህ፣ ድጋፉ ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዝ ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍ መሆኑን በሕክምና መሣሪያዎቹ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።

ድሬዳዋ እና ኩንሻን ከተሞች ወዳጅነት የመሠረቱት እ.አ.አ በ2018 ሲሆን በተለያዩ ፕሮከጅቶች ሥራ ላይ በትብብር እየሠሩ ነው ሲል ሽንዋ ዘግቧል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top