Connect with us

ደቡብ ኮርያ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የህክምና ቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ አደረገች

ደቡብ ኮርያ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የህክምና ቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ አደረገች
Photo: Facebook

ጤና

ደቡብ ኮርያ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የህክምና ቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ አደረገች

የደቡብ ኮርያ መንግሥት ከአገሪቱ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውሉ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገች።

ድጋፉ 28 ሺህ 33 የመመርመሪያ ኪቶች፣ 150 ሺህ 400 የፊት ጭንብል፣ 60 ሺህ ዶላር የሚያወጣ የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮችን ያጠቃልላል።ጎን ለጎንም ለኮሮናቫይረስ መከላከል የሚውል ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ሁን ሚን ሊም እንደተናገሩት፤ የኮርያ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ከኢትዮጵያ ጋር ይተባበራል።

ኮርያ በዓለም ደረጃ አሳሳቢ የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የምታከናውናቸውን በጎ ተግባራትና ልምድ ለኢትዮጵያ ታካፍላለች ብለዋል።

በዚህ ላይ ያለውን አጋርነት በተለይም በኢንተርኔት በመታገዝ እንደምታጠናክር ገልጸው፤ በቀጣይም ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ድጋፍ በሚያስፈልጋት ሁሉ ኮርያ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደሩ ተናግረዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፤ ድጋፉ በአገር አቀፍ ደረጃ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ሥራ ያጠናክራል ብለዋል።
የኮርያ መንግሥት በኮሮና ቫይረስ መከላከል ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የጤና ዘርፍ ሥራዎች ላይ አጋር መሆናቸውን ገልጸዋል።
በደቡብ ኮርያ የተደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አምባሳደሩ ቃል መግባታቸውን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 261 ደርሷል፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 106 ሲሆኑ 5 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው ይታወሳል።

ኢዜአ  አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2012

Continue Reading
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top