Connect with us

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የምግብ እጥረት እንዳያጋጥም ….

የምግብ እጥረት እንዳያጋጥም ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ይመረታል… የግብርና ሚኒስቴር

ዜና

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የምግብ እጥረት እንዳያጋጥም ….

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የምግብ እጥረት እንዳያጋጥም ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ይመረታል… የግብርና ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የምግብ እጥረት እንዳይፈጠር ከመኸር ምርት በተጨማሪ 40 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል እንደሚመረት የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ገለጹ። እንደሚኒስትሩ ገለፃ 50 ሚሊዮን ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬም ማምረት ተጀምሯል።

የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ ምርትና ምርታማነት እንዳይቀንስ ከመደበኛው የእርሻ እንቅስቃሴ በተጨማሪ ምርት የሚጨምሩ ተግባራት እያከናወኑ መሆኑን አቶ ዑመር ሁሴን ለኢዜአ ተናግረዋል።

”የበሽታው ስርጭት በዚሁ ከቀጠለ፣ ምናልባትም ከውጭ የሚገቡት የስንዴ ምርት ቢቆምና አምስት በመቶ ምርት ቢቀንስ የሚል ግምት ወስደን ያንን ሊተካ የሚችል እቅድ አውጥተን እየሰራን ነው” ብለዋል።

በዚህም ዘንድሮ በመኽር ወቅት እርሻ በተጨማሪ 40 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማምረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
እንዲሁም 50 ሚሊዮን ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ የሚመረትበት እንቅስቃሴ መጀመሩን አቶ ዑመር አስታውቀዋል።

በሥራው ለከተማ ግብርና ትኩረት መሰጠቱን ያመለከቱት ሚኒስትሩ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የእንሰሳት ሃብት፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራዎች ከማዕከል በተመደቡ ባለሙያዎች ተጀምረዋል ነው ያሉት።

የከተማ ግብርና ለኮሮና ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን፤ባለፈው በጀት ዓመት የወጣውን ፖሊሲ በመተግበር እንደሚስፋፋም ተናግረዋል።

ለበልግ ወቅት ምርት ወደ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር የሚሆን መሬት ታርሶ 64 በመቶው ዘር መልበሱን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ ለመኸር ወቅት እርሻ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ከውጭ በመግባት ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

የአገሪቷ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ዘመናዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱንም አመልክተዋል። ምንጭ :-ኢቢሲ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top