Connect with us

የግብፅ መረጃዎች አብዛኛዎቹ የተደራሲውን አስተሳሰብ ለማዛባት የታለሙ ናቸው

‹‹የግብፅ መረጃዎች አብዛኛዎቹ የተደራሲውን አስተሳሰብ ለማዛባት የታለሙ ናቸው››

ኢኮኖሚ

የግብፅ መረጃዎች አብዛኛዎቹ የተደራሲውን አስተሳሰብ ለማዛባት የታለሙ ናቸው

‹‹የግብፅ መረጃዎችም ሆኑ ሪፖርቶች አብዛኛዎቹ የተደራሲውን አስተሳሰብ ለማዛባት የታለሙ ናቸው›› ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና

ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ያዕቆብ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ በግብፅ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የተመለከቱ መረጃዎች በከፍተኛ ሁኔታ ይሰራጫሉ። በርካታ መግለጫዎችም ይወጣሉ። አብዛኛዎቹ መረጃዎችም ሆኑ ሪፖርቶች የአንባቢውን ወይም የአድማጩን አስተሳሰብ ለማዛባት የታለሙ ናቸው።

የሚሰራጩት መረጃዎች የአድማጩን አስተሳሰብ ለማዛባት ሆነ ተብለው የሚነገሩ እንደሆኑ የገለጹት ፕሮፌሰር ያዕቆብ፣ ይህ አስተሳሰብን ለማዛባት የሚደረገው አካሄድ በጋዜጣዊ፣ በዲፕሎማሲያዊ እንዲሁም በፖለቲካዊ መስመር ብቻ ሳይወሰን በአካዳሚክ እና በሳይንስ ነክ ሪፖርቶችም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮፌሰር ያዕቆብ የግብፅን ድርጊት ለመወዳደር ጥረት ማድረግ አስፈላጊ እንዳልሆነ ፤ ግብፅ እንደምታደርገው
ሁሉ ኢትዮጵያም ይህንን ማድረግ እንደማይጠበቅባት፤ በኢትዮጵያ በኩል ትክክለኛ አቋሞችንና ማስረጃዎችን በተሻለ ፍጥነት እንዲሁም በስፋት ማድረስና የተሻለ ታታሪነት ከመንግሥትም ሆነ ከሌሎች ወገኖች እንደሚ ጠበቅ አስረድተዋል።

እንደ ፕሮፌሰር ያዕቆብ ገለጻ፤ ግብፅ የትብብር አስተሳሰብ እና የትብብር ማዕቀፍን የማደናቀፍ አካሄዷ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ብዙ ትርፍ አያስገኝላትም። ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች የውሃ አመንጪ አገሮች በቀና መሰረት ላይ የጸና የጋራ ስምምነት እንዲኖራቸው ግብፅ አለመፈለጓ የማደናቀፍ አባዜ ስለተጠናወታት እንጂ ሌሎቹ አገሮች የውሃ ልማቱን ለብሄራዊ ጥቅማቸው ሲሉ ይቀጥሉበታል።

ፕሮፌሰር ያዕቆብ፣ የትብብር ማዕቀፉን ግብፅ ማደና ቀፍ የተያያዘችው ገና በስድስቱ አገሮች ከመፈረሙ በፊት እንደነበር አስታውሰው፤ ይህ አካሄድ ግብፅን ከቆየው የሞኖፖሊ ይዞታዋ ስለሚያስለቅቃት የማዕቀፍ ሰነዱን አበክራ እንደምትጻረር ተናግረዋል።

አዲስ ዘመን ሚያዝያ 27/2012

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top