Connect with us

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ተስተጓጎለ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ተስተጓጎለ
Image credited Teshager Tassew

ዜና

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ተስተጓጎለ

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር መስመር ላይ የተሽከርካሪ አደጋ በመድረሱ አገልግሎቱ ተስተጓጎለ

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው የባቡር መስመር መሰረተ ልማት ላይ አደጋ በማጋጠሙ የትራንስፖርት አገልግሎቱ መስተጓጎሉ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት የትራንስፖርት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ ቦጋለ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዛሬ እኩለ ቀን የባቡር መስመሩ ላይ የተሽከርካሪ አደጋ ደርሷል።

አደጋው ሳሪስ ልዩ ስሙ ሬይስ ኢንጂነሪንግ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ኮንቴይነር የጫነ ከባድ ተሽከርካሪ በባቡር ሐዲድ መሰረተ ልማቱ ላይ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።

በዚሁ ሳቢያም ከሳሪስ አቦ ወደ ስቴዲየም ከስቴዲየም ወደ ሳሪስ አቦ የሚደረገው የባቡር ምልልስ በጊዜያዊነት መቋረጡን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት ችግሩን ለመፍታትና መስመሩን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ነው ያመለከቱት።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top