Connect with us

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለካፒ የወርቅ ማዕድን ኃይል ለማቅረብ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጊምቢ ቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
Photo Facebook

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለካፒ የወርቅ ማዕድን ኃይል ለማቅረብ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጊምቢ ቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጊምቢ ቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል ባለ 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ እና ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የሲኖ ሃይድሮ ኩባንያ ተወካይ ሚስተር ቲያን ሆንጉአን ናቸው የተፈራረሙት።

መንግሥት ለዚህ ፕሮጀክት ልዩ ትኩረት በመስጠት የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ወጪ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሸፈን ማድረጉን ኢ/ር አሸብር ተናግረዋል።

የወርቅ ማዕድኑ ከሚያስገኘው የውጭ ምንዛሬ አንጻር የፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ጥራቱን ጠብቆ መጠናቀቅ እንዳለበትም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አሳስበዋል።

የሥራ ተቋራጩ ተወካይ ሚስተር ቲያን በበኩላቸው፣ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት ስለተገነዘብን ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ እና ጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እንሠራለን ብለዋል። ለፕሮጀክቱ ግንባታ 5 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እና 121 ሚሊየን ብር በጀት ተይዞለታል።

ፕሮጀክቱ አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና 40 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ባለ 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታን ያጠቃልላል ተብሏል።

አጠቃላይ ግንባታውም በ13 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top