Connect with us

በኢትዮጵያ 2 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ 2 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
Photo Facebook

ጤና

በኢትዮጵያ 2 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ 2 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
—-
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው ብሔራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የእስካሁን አፈፃፀሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ተገምግሟል።

የኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረቡት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 912 የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም ኢትዮጵውያን ወንዶች ናቸው።

አንደኛው ከኬንያ የተለመሰና በሞያሌ ለይቶ ማቆያ የነበረ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን ሁለተኛው ከፑንትላንድ የተመለሰ እና በጂግጂጋ ከተማ ለይቶ ማቆያ የነበረ የ20 ዓመት ወጣት ነው። የዛሬዎቹን ጨምሮ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 133 ደርሷል።

Worldwide
  • Country
    Cases
    Deaths
    Recovered
Total
0
0
0

በሌላ በኩል 7 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ደርሷል።

በሀገሪቱ እስካሁን ለ18,754 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርምራ መደረጉም ተገልጿል።

Ethiopia

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top