Connect with us

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሰራተኞች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ድንገተኛ ምርመራ የተደረገላቸው 2 የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሰራተኞች ኮቪድ-19 ተገኘባቸው!
Photo Facebook

ዜና

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሰራተኞች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ድንገተኛ ምርመራ የተደረገላቸው 2 የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሰራተኞች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!

በጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር ድንገተኛ ምርመራ የተደረገላቸው የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው ሁለት (2) ቻይናዊያን ሲሆኑ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ሹፌሮች ናቸው።

ከሁለቱ (2) ቻይናዊያን ጋር በስራቸው ምክንያት ቅርበት ያላቸው 35 የምድር ባቡሩ ሰራተኞች ተለይተው የምርመራ ናሙና ተወስዶላቸዋል።

የኢትዮ – ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ጥላሁን ሳርካ ለሸገር ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ‘የናሙና ውጤቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ይደርሳል ብለን እየጠበቅን ነው’ ብለዋል።

ወደ ጅቡቲ ባቡር እየዘወሩ የሚሄዱ ሰራተኞች ደርሰው ሲመለሱ ‘ከሙቀት መለኪያ’ በስተቀር ተጨማሪ ምርመራ አካሂደው እንደማያውቁ ኢንጂነር ጥላሁን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

በሸገር ኤፍ ኤም 102.1

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top