Connect with us

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በከተማ አስተዳደር ላይ የግልጽነት ጥያቄ አቀረበች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የግልጽነት ጥያቄ አቀረበች
Photo Facebook

ዜና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በከተማ አስተዳደር ላይ የግልጽነት ጥያቄ አቀረበች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የግልጽነት ጥያቄ አቀረበች፡፡

በዲዛይኑ ላይ የሚታየው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ዛፎች ግልጽ ስፍራ መሆን ከሚፈልገው አደባባይ ጽንሰ ሀሳብ ጋር ይቃረናል የሚሉ ወገኖችም አስተያየታቸውን እያቀረቡ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ወንዞች ልማት ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚሰራቸው የማስዋብና የማሳመር ስራዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የግልጽነት ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡

በማህበረ ቅዱሳን ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ ይፋ በሆነው መረጃ መሰረት በአባ ያሬድ የመንበረ ፓትረያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያና የአርሲ ሀገረ ስብክት ሊቀ ጳጳስ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ ቤተክርስቲያኗ ስምምነቷ ሳይጠየቅ የጃን ሜዳን ታሪካዊ የበዓለ ጥምቀት ሥርዓት ማከናወኛ ስፍራ ለገበያነት የማዋል ጉዳይ እንዳሳዘናት ገልጻለች፡፡

 

ከዚህ በሻገር በመስቀል አደባባይ የሚሰራው ፕሮጀክትም በቤተ ክርስቲያኗ እውቅና የሌለው መሆኑን ነው ደብዳቤው የሚያስረዳው፡፡ ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት የተጻፈው ደብዳቤ በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ ለቤተክርስቲያኗ መልስ እንዲሰጥም ይጠይቃል፡፡

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በመስቀል አደባባይ የሚሰሩ የልማት ስራዎች መልካም ሆነው ሳለ በማስዋብና በማልማቱ ተግባር የሚተከሉት ዛፎች ስፍራው የሚፈልገውን ግልጽ የመሆን አደባባይነት የሚቃረንና በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል በዓል ማክበሪያ እንደመኾኑ የእይታ ችግር ሊገጥም እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ተቁመዋል፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top