Connect with us

በድሬዳዋ ከባድ ዝናብ የአራት ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ

በድሬዳዋ ከባድ ዝናብ የአራት ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ
Photo: Social media

ዜና

በድሬዳዋ ከባድ ዝናብ የአራት ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ

በድሬዳዋ ከባድ ዝናብ የአራት ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ

በድሬዳዋ ትናንት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍና የቤት መደርመስ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ንብረት ማውደሙን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ ።

የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት እና የለውጥ ስራዎች ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ እንደገለፁት ትናንት እኩለ ቀን ላይ በአዲስ ከተማ ገንደ ቁጭ በተባለው ሰፈር ለሁለት ሰዓታት የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ሁለት ሰዎች በጎርፍ ሁለት ሰዎች ደግሞ በመኖሪያ ቤት መደርመስ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ።

በዝናብ የራሰ ቤት ተደርምሶ ተኝተው የነበሩ የሁለት ወርና የአራት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናት በፍርስራሹ ታፍነው ህይወታቸው አልፏል ።

ሌላዋ የሁለት ዓመት እህታቸው ከባድ ጉዳት ደርሶባት ወደ ድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል መወሰዷ ተገልጿል።

አንዲት የ19 ዓመት ወጣትና የ45 ዓመት ጎልማሳ በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ሲያልፍ በፍለጋ አስከሬናቸው ወጥቶ ለጊዜው በድረዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል እንዲያርፍ ተደርጓል።

ተጨማሪ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሱንም ኮማንደሩ ገልፀዋል።

በጎርፍ ተወስደው ከነበሩ 4 ባለ ሶስት እግር ባጃጆች መካከል ሶስቱ በፍለጋ የተገኙ ሲሆን አራተኛው ገና አልተገኘም።

የጎርፍ አደጋው በርካታ የመኖሪያ ቤቶችና መሰረተ ልማቶች ያፈራረሰ ሲሆን የጉዳት መጠኑ በመጠናት ላይ ነው ተብሏል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሃር የተመራው የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላትና ሌሎችም አመራሮች ጎርፍ ባጋጠመበት አካባቢ ተገኝተው ተጎጂዎችን አፅናንተዋል።

ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተወስዳ የነበረችው የሁለት ዓመት ህፃን በተደረገላት የህክምና ዕርዳታ ጤንነትዋ መሻሻል ማሳየቱን በድል ጮራ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ባለሙያ ነርስ ታሪኩ ታደሰ ገልፀዋል።(ኢኘድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top