Connect with us

የቻይና በረራ አለማቋረጣችን ትክክል ነበርን ~ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ

የቻይና በረራ አለማቋረጣችን ትክክል ነበርን ~ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
GETTY IMAGES

ኢኮኖሚ

የቻይና በረራ አለማቋረጣችን ትክክል ነበርን ~ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ

የቻይና በረራ አለማቋረጣችን ትክክል ነበርን ~ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ

በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኮሮናቫይረስ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ ድርጅታቸው ወደዚያ ሲያደርግ የነበረውን በረራ አለማቋረጡ ትክክል እንደነበር ተናገሩ።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተወልደ ገብረማሪያም ለቢቢሲ እንደተናገሩት በንግድ ግንኙነት ምክንያት ከቻይና ጋር ጥብቅ ቁርኝት ላላቸው የአፍሪካ አገራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወሳኝ አገልግሎትን ሰጥቷል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አየር መንገዳቸው በቀጥታ በረራና በኮቪድ-19 ስርጭት መካከል ግንኙነት አለው ብሎ እንደማያምንም ተናግረዋል።

ጨምረውም በጣም ጠበቅ ያለ የጉዞ ቁጥጥርና እገዳዎችን ባወጡ አገራት ውስጥ ሳይቀር ወረርሽኙ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አመልክተዋል።

ነገር ግን በረራዎችን በማገድ በኩል በምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታዎችና በሕዝብ ጤና መካከል ሚዛን መጠበቅ ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለበት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይና ውስጥ በሽታው ተስፋፋፍቶ በነበረበት ወቅት ቤይጂንግና ሻግሃይን ወደመሳሰሉ ከተሞች በረራ ያደርጉ ከነበሩ የተወሰኑ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነበር።

በሽታው በመላው ዓለም ከተሰራጨ በኋላ ክፉኛ ተጽዕኖውን ካሳረፈባቸው ዘርፎች መካከል የአየር ትራንስፖርት አንዱ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከፍ ያለ ኪሳራ እንዳጋጠመው ተነግሯል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ጊዜ ካለው አቅም በ10 በመቶ ብቻ እየሰራ ሲሆን ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማጣቱን ሮይተርስ በቅርቡ ዘግቦ ነበር።

አቶ ተወልደ የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ በወረርሽኙ ምክንያት የገጠመውን ፈተና በተመለከተ ሲናገሩ፤ ድርጅታቸውን በዚህ የቀውስ ወቅት ይዞ መራመድ ፈታኝ ቢሆንም ጭነት በረራዎችን በመጨመር በመንገደኞች ጉዞ ያጣውን ገቢ ለማካካስ እየሞከረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቶበት በነበረበት ወቅት ጥቂት ያማይባሉ አየር መንገዶች ወደ ቻይና ያደርጓቸው የነበሩ በረራዎችን አቁመው ነበር።

በዚህም ሳቢያ በርካቶች ወረርሽኙን በመፍራት የኢትዮጵያ አየር መንገድም ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች እንዲሰርዝ ግፊት ሲያደርጉበት ቆይተዋል።

BBC

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top