Connect with us

የሕዳሴው ግድብ የብረታብረት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ

የሕዳሴው ግድብ የብረታብረት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ
Photo: DireTube

ኢኮኖሚ

የሕዳሴው ግድብ የብረታብረት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ

የሕዳሴው ግድብ የብረታብረት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የብረታብረት ፍሬም ሥራ 100 % የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የሲቪል ሥራው 87 በመቶ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው ደግሞ 46 በመቶ መጠናቀቁን የሕዳሴው ግድብ ሥራ አስኪያጅ ተናገሩ።

ሥራ አስኪያጁ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ሥጋት በዓለም ላይ ጥላውን ያጠላ ቢሆንም የሕዳሴው ግድብ ሥራ በነበረው ግለት እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም 73 በመቶ መድረሱንም ገልጸዋል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሠራተኞችን በመጠበቅ የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ሥራው ያለ አንዳች እንከን መቀጠል እንዲችል እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት ኢንጂነር ክፍሌ፣ ከግብዓት አቅርቦት ጋር በተያያዘም ችግሮች እንዳይገጥሙ ታቅዶበት እየተሠራ እንደሆነ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስታውቀዋል፡፡

ግድቡ በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ላይ ኃይል ማመንጨት እንዲችል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ኢንጂነር ክፍሌ፣ የውሃ ሙሊቱ በሚቀጥለው የክረምት ወራት እንደሚጀምርና እቅዱን በሚገባ ማሳካት በሚቻልበት ቁመና ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top