Connect with us

የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎቹ የመተንፈሻ አጋዥ መሣሪያ ሰርተው በሙከራ ሒደት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ

የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎቹ የመተንፈሻ አጋዥ መሣሪያ ሰርተው በሙከራ ሒደት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎቹ የመተንፈሻ አጋዥ መሣሪያ ሰርተው በሙከራ ሒደት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ

የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎቹ የመተንፈሻ አጋዥ መሣሪያ ሰርተው በሙከራ ሒደት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ

N.E.R.D – (New era research &developmet Center) የተሰኘ የግል ኩባንያ በተለይ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ለታማሚዎች አገልግሎት ሊውል የሚችል የመተንፈሻ አጋዥ መሣሪያ (መካኒካል ቬንትለተር) ሰርቶ በሙከራ እና ዲዛይኑን በማሻሻል ሒደት ውስጥ እንደሚገኝ አስታወቀ።

ድርጅቱ በዋንኛነት የሆስፒታሎችን የኮምፒውተር ሲሰተም በመስራት ባለፉት አምስት ዓመታት ልምድ ማካበቱን ተናግረው በተለይ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ እንደአገር ያጋጠመውን የመተንፈሻ አጋዥ መሣሪያዎች እጥረት ለመቅረፍ በአገር አቀፍ ዕውቀታቸውን አስተባብረው ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ የትምህርት ባክግራውንዳቸው የኮምፒውተር ሳይንስ በመሆኑ መሣሪያውን በመሥራት ሒደት የተለያዩ አስተያየቶችን ለማሰባሰብ በማህበራዊ ድረገፃች ግሩኘ መመስረታቸውን እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች አስተያየቶችን በየጊዜው እየተቀበሉ ማሽኑን በሙከራ ሒደት የማሻሻል ሒደቶችን እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ እንደተናገሩት ለሙከራ በአሁን ሰዓት ተሰርቶ የቀረበው የመተንፈሻ አጋዥ መሣሪያ በጤና ባለሙያዎች አስተያየቶች በየጊዜው እየተሰጠበት እየተሻሻለ የመጣ ነው። ኘሮጀክቱን በመሥራት ሒደት የግልና የመንግሥት ተቋማትና ግለሰቦች ገንቢ የሀሳብ ድጋፍ እንዳደረጉላቸውም ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት ለሙከራ የተሰራው ማሽን ለሁለትና ለሶስት ቀናት ያለማቋረጥ እንዲሰራ ተደርጎ ውጤታማ ሆኗል ብለዋል።
ማሽኑ በቀላሉ በአገር ውስጥ በሚገኙ አልሙኒየም እና ፒቪሲ በመሳሰሉ ማቴሪያሎች መሰራቱን ተናግረው እነዚህን መሳሪያዎች የሚያዘጋጁ አካላት በዲዛይኑ መሰረት በቀን 500 ምርት ማዘጋጀት እንደሚችሉ አረጋግጠውልናል ብለዋል።
የፈጠራ ሥራውን ለኢኖቬንሽን ሚኒስቴር መላካቸውን የፈጠራ ባለሙያዎቹ አስታውሰው ግብረመልስ እየጠበቁ መሆኑን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ አጋዥ የመተንፈሻ መሣሪያ ጠቅላላ ቁጥር ከ500 በታች መሆኑ፤ የኮሮና ወረርሽኝ ቢጠናከር ምን እንሆናለን የሚል ከባድ ሥጋትን በአገር ደረጃ መፍጠሩ የሚታወቅ ነው።

የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም ዶ/ር ሰኢድ አራጌ እንደሚሉት በኢትዮጵያ አለ የሚባለው የመተንፈሻ ማሽኑ ኮሮና ሳይኖር በሌላ አይነት ታካሚዎች የተያዘ ነው በማለት እነዚህ ታካሚዎች የት ይሄዳሉ? ሲሉ ይጠይቃሉ።

አያይዘውም ሁሉንም እንርሳቸው ለኮሮና የሚሆን ምንም መካኒካል ቨንቲሌቴር የለንም። ያለን ዜሮ አካባቢ ነው” በማለት የችግሩን አሳሳቢነት ፅፈዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top