Connect with us

የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ

ጥበብና ባህል

የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለቦርን አጌን በጎ አድራጎት ድርጅት የንፅህና መጠበቂያ ፈሳሽ እና ደረቅ ሳሙና ድጋፍ አደረገ፡፡

አቶ ሙሉጌታ ተፈራ የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ከቢሮው ጋር የሚሰሩ በከተማችን 65 የሚሆኑ በበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማሩ ተቋማት ያሉ መሆናቸውን ገልፀው ይህም ድርጅት አንዱ ሲሆን መቶ የአይምሮ ህሙማን በመንከባከብ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ሙሉጌታ ገለፃ ቢሮው ከዚህ በፊት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ ድጋፍ ማድረጉንና የዛሬው ድጋፍ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

በተያያዘ ዜና ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለቦርን አጌን በጎ አድራጎት ድርጅት የምሳ እና የሳኒታይዘር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የቦርን አጌን የበጎ አድራጎት ድርጅት ከውጭ እና ከሀገር ውስጥ በሚያገኘው ድጋፍ ጎዳና ላይ የወደቁ የአይምሮ ህሙማንን ከጎዳና ላይ በማንሳት የምግብ፣ የመጠለያ እና የጤና ድጋፍ የሚያደርግ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡

ምንጭ:- የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህራዊ ጉዳይ ቢሮ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top