Connect with us

የመዘዋወር ነጻነትን በተመጣጣኝ መንገድ ብቻ መገደብ ያስፈልጋል

"የመዘዋወር ነጻነትን በተመጣጣኝ መንገድ ብቻ መገደብ ያስፈልጋል"
Photo Facebook

ዜና

የመዘዋወር ነጻነትን በተመጣጣኝ መንገድ ብቻ መገደብ ያስፈልጋል

“የመዘዋወር ነጻነትን በተመጣጣኝ መንገድ ብቻ መገደብ ያስፈልጋል” – የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል በፌዴራልም ሆነ በክልል መንግስታት በመዘዋወር ነፃነት እና በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚጣል ማናቸውም አይነት ገደብ የሰብዓዊ መብቶች መርህን የተከተለ መሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የሚኒስትሮች ኮሚቴ ሚያዝያ 9 ቀን ያወጣው የትራንስፖርት ክልከላ አካላዊ መቀራረብንና ጠቅላላ እንቅስቃሴዎችን ለመቀነስ አስፈላጊ እርምጃዎች ቢኖሩትም፤ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ አለመሰጠቱና የተወሰኑት ገደቦች የተፈለገውን አላማ ከማሳካት አንጻር አስፈላጊነታቸው ጥያቄ ያስነሳል ሲል ነው የገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደም ብሎ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንዲሁም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በድንገት ታግዶ የነበረው የትራንስፖርት እገዳ ድንገተኛ ስለነበር በህብረተሰቡ ላይ እንግልት መፍጠሩን ነው አስታውሷል፡፡

የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥት የሚወስዱት የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃ በሕገ መንግሥቱና በዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ግዴታዎችና መርሆች መሰረት የተመራ ሊሆን እንደሚገባና ያስፈለገበትን ዓላማ ለማሳካት እጅግ አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ እና ለነገሩ ሁኔታ በጥብቅ ተመጣጣኝ እርምጃ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው ሲል ነው የገለጸው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top