Connect with us

እናስተውል

እናስተውል
Photo: Social media

ጤና

እናስተውል

እናስተውል | (ዶ/ር አለማየሁ አረዳ)

ዛሬ በዓለማችን ኮቪድ 19ን ለመከላከል የሚረዱ ምክሮች ይጎርፋሉ።
እኔን ያስጨነቀኝ ይህ ሁሉ ምክር አእምሮ ላይ የሚፈጥረው ጫና ነው።
ከበርካታ ምክሮች መሃል ጥቂቱን አበክረን ብንይዝ አእምሮአችን ሳይጨነቅ በመጠንቀቅ መከላከል የሚቻል ስለመሠለኝ እነዚህን ጠቃሚ ነጥቦች ማቅረብ ፈለግሁ። አትሠልቹ ተመልከቱት።

1 አእምሮአችንን የመረጃ ቋት አናድርገው!!
አገኘን ብለን ከልዩ ልዩ ምንጭ በልዪ
ልዩ መንገድ የምንሠበስበው መረጃ
አእምሮአችንን ያስጨንቀዋል። እናም
ተገቢ መረጃ ከተገቢ ምንጭ!!

2 ፍርሃትን መለየት
ስጋትና ጭንቀት የሚያበረታ ፍርሃት
አይጠቅምም
ጥንቃቄን የሚያጎለብት ከሆነ ጥሩ ነው

3. ሌሎችን ማየት
በተለይ ከኛ ባነሰ ደረጃ ያሉትን
አስተውለን ባገዝን መጠን
የመንፈስ ብርታት ይሠጠናል።

4. ከሌሎች መማር
ጭንቀትን ሳይሆን ብርታትን ከታጠቁ
ሰምቶ መማር

5 ሙዚቃ ይጠቅማል
መንፈሳዊም ይሁን ዓለማዊ ለሰለስና
ጣፈጥ ባለ ይዘቱ መንፈስ ይጠግናል

6 አዝናኝ ጽሁፎችና ፊልሞች ይረዳሉ
በተለይ ኮሚዲ ምትሀት አለው

7. ቀላል አካላዊ እንቅስቃሴ አእምሮን
የማስደሰት አቅም አለው።

በመጠንቀቅ ተከላክለን እንረታዋለን!
በቸር ቆዩኝ!
ምርጥና ልዩ ፋሲካ ይሆናል!!!

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top