Connect with us

ኢትዮ ቴሌኮም የቤት ቆይታን የሚያበረታታ የዳታ እና የድምፅ ቅናሽ ጥቅል ፓኬጆችን አዘጋጀ

ኢትዮ ቴሌኮም የቤት ቆይታን የሚያበረታታ የዳታ እና የድምፅ ቅናሽ ጥቅል ፓኬጆችን አዘጋጀ
Photo: Social media

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ኢትዮ ቴሌኮም የቤት ቆይታን የሚያበረታታ የዳታ እና የድምፅ ቅናሽ ጥቅል ፓኬጆችን አዘጋጀ

ኢትዮ ቴሌኮም የቤት ቆይታን የሚያበረታታ የዳታ እና የድምፅ ቅናሽ ጥቅል ፓኬጆችን አዘጋጀ

ኢትዮ ቴሌኮም በሚሰጣቸው የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ከነገ ጀምሮ ማሻሻያ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በሰጡት መግለጫ፥ ዜጎች እንቅስቃሴያቸውን በመገደብ በቤታቸው እንዲቆዩ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ ማሻሻያ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በዚህም “በቤትዎ ይቆዩ” የሞባይል ጥቅል አገልግሎት፣ የተለያዩ ድረ ገጾችን በነጻ መጎብኘት የሚያስችል አገልግሎት እንዲሁም የቅድመ ክፍያ ሞባይል አየር ሰአት የቆይታ ጊዜን የሚያራዝም አገልግሎት ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው ያሉት።

ይህን ተከትሎም በቤትዎ ይቆዩ የሞባይል ድምጽ ጥቅል አገልግሎት ደንበኞች በ5 ብር 30 ደቂቃ የሃገር ውስጥ የድምጽ ጥሪ 20 ነጻ የአጭር የፅሁፍ መልዕክት መጠቀም ይችላሉ።

በተጨማሪም በቤትዎ ይቆዩ የሞባይል ኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት በ5 ብር 100 ሜጋ ባይት ኢንተርኔት እንዲሁም 20 ነጻ የአጭር የሃገር ውስጥ የፅሁፍ መልክት እንዲሁም በ10 ብር 250 ሜጋ ባይት ኢንተርኔት እና 20 ነጻ የሃገር ውስጥ አጭር የፅሁፍ መልዕክት መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በቤትዎ ይቆዩ የሞባይል ኢንተርኔት እና ድምጽ ጥቅል አገልግሎት ደግሞ ደንበኞች፥ በ15 ብር 300 ሜጋ ባይት ኢንተርኔት እና 30 ደቂቃ የሃገር ውስጥ የድምጽ ጥሪ ከ20 ነጻ የሃገር ውስጥ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ጋር።

ደንበኞች እነዚህን አገልግሎቶች ከማለዳው 12 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፥ ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ ግን በነበረው መደበኛ ታሪፍ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።(ፋና)

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top