Connect with us

እርድን በተመለከተ የሚኒስትሯ የዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት

እርድን በተመለከተ የሚኒስትሯ የዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት
Photo Facebook

ዜና

እርድን በተመለከተ የሚኒስትሯ የዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት

እርድን በተመለከተ የሚኒስትሯ የዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት:-
~በግብይት ወቅት እንስሳትን መነካካት ቢቀር፣
~ ጥሬ ሥጋ መብላት አንመክርም፣
***

“…እስካሁን ባለው መረጃ ቫይረሱ ከሰው ወደ እንስሳት ሊተላለፍ ስለሚችል በግብይት ወቅት የሚደረጉ ልማዳዊ እንስሳትን የመነካካት ተግባር ቢቀር መልካም ነው።

በእርድ ወቅትም በተቻለ መጠን ባለቤት ቢያርድ መልካም ነው፤ ካልተቻለ ግን በቄራዎች ቢደረግ መልካም ነው።

በእርድ በባለሙያ የሚከናውን ከሆነ ግን ደህንነትና ጥንቃቄ በተሞላ መልኩ ሊከናወን ይገባል፤ በዚህም እርድ ለሚያከናውነው ባለሙያ የእጅ ጓንት እና የአፍ መሸፈኛ ማዘጋጀት የግድ ነው።

እርዱ በጋራ የሚከናወን ወይም ቅርጫ ከሆነ ደግሞ ከተቻለ ባለቤቱ አሊያም ደግሞ ጥቂት ሰዎች በተገኙበት ብቻ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መከናወን አለበት። ይህንንም በእያንዳንዱ ሂደት እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ እንዲሁም የእጅ ጓንት እና የአፍ መሸፈኛ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ቫይረሱ ሥጋን በመብላት ከእንስሳት ወደ ሰው ይተላለፋል የሚለው የተሳሳተ እና እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘለትም።

ጥሬ ሥጋን መብላትን አንመክርም። ሥጋው የግድ መብሰል አለበት፤ የበሰለ የእንስሳት ተዋዕፆ ከጤናም አንፃር አስፈላጊውን አቅም ስለሚሰጠን መመገብ ጠቃሚ ነው።”

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top