Connect with us

ዱባይ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ ወደ ኢትዮዽያ መላኳ ተሰማ

ዱባይ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ ወደ ኢትዮዽያ መላኳ ተሰማ
Photo: Social media

ዜና

ዱባይ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ ወደ ኢትዮዽያ መላኳ ተሰማ

ዱባይ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ ወደ ኢትዮዽያ መላኳ ተሰማ

ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 33  ሜትሪክ ቶን ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የህክምና ቁሳቁሶችን የያዘ አዉሮፕላን ከዱባይ ተነስቶ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መላኩን ኤምሩትስ ኒዉስ ኤጀንሲ የተሰኝ የሀገሪቱ የዜና ተቋም ዘግቧል፡፡

ከድጋፍ ቁሳቁሶቹ ዉስጥ 15 ሜትሪክ ቶን የሚሆነዉ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለኢትዮዽያ የተሰጠ ሲሆን 3 ሜትሪክ ቶን የሚሆነዉ ደግሞ ለአፍሪካ ህብረት የተደረገ ድጋፍ ነዉ፡፡ ቀሪዉ 15 ሜትሪክ ቶን ሚሆነዉ የህክምና ቁሳቁስ ከአለም የጤና ድርጅት በአፍሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ስራ እንዲዉል የተላከ መሆኑን ዘገባዉ አክሏል፡፡

ድጋፉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት በአለም ላይ እየተካሄደ ያለዉን ጥረት ለማገዝ ካላት ፍለጎት የመነጨ እንደሆነም ታዉቋል፡፡

እንዲህ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሰብዓዊ ድጋፎችን እንደየአስፈላጊነታቸዉ የማቅረብ ቁርጠኝነቱ እንዳላት በኢትዮዽያ የዱባይ አምባሳደር መሀመድ ሳሌም አል ረሻድ በዕለቱ መግለፃቸዉን ያሰፈረዉ ይህ ዘገባ ለኢትዮጲያ የተደረገዉ ድጋፍ የህክምና ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት በሚዲርጉት ሂደት ዉስጥ ደህንነታቸዉ እንዲጠበቅ ያግዛል ማለታቸዉን አክሎ ገልፃል፡፡

ይህንን በሰዉ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለ መከራ ለመግታት በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ የሀገሪቱ መንግስትና ህዝብ ከኢትዮጲያና ከሌሎች በቫይረሱ ጉዳት ከደረሰባቸዉ የዓለም ሀገራት ጋር ለመቆም ችግሩን ለመቀነስ እንደሚሰራ አምባሳደሩ መግለፃቸዉም በዘገባዉ ተነስቷል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top