Connect with us

የመሬት ባንከ እና ልማት ኮርፖሬሽን ከአርክቴክቶች ማህበር ጋር ለመስራት ተፈራረመ

የመሬት ባንከ እና ልማት ኮርፖሬሽን ከአርክቴክቶች ማህበር ጋር ለመስራት ተፈራረመ

ዜና

የመሬት ባንከ እና ልማት ኮርፖሬሽን ከአርክቴክቶች ማህበር ጋር ለመስራት ተፈራረመ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የመሬት ባንከ እና ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ጋር በመሬት ይዞታ ልማት እና በዘርፉ ዕድገት ዙሪያ ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የወቅቱን ኮቪድ-19 ወረርሽኝን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል የመግባቢያ ስምምነት ፊርማው በቪዲዮ ኮንፍረንስ በመታገዝ በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ት ሌንሳ መኮንን እና በኢትዮጵያ አርክትቴክቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል መኮንን መካከል ተፈርሟል፡፡

በሰዎች እንቅስቃሴ አልያም በራሳቸው ዕድገት በመነጨ የኢትዮጵያ ከተሞች በፈጣን የከተማነት ሂደት ውስጥ ያሉ ሲሆኑ፤ ይህም በፍጥነት እያደገ ያለው የከተማ ቅየሳ እና ንድፍ ፍላጎቱን ተደራሽ ባደረገ መልኩ መከናወን እንዳለበት ያመላክታል፡፡ ከዚህ አንጻር የመሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን በፌደራል መንግሥት ተቋማት እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስር ያሉ የመሬት ይዞታዎችን በመለየትና በማልማት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል እዲሁም ተለዋዋጭ ከሆነው የመሬት ልማት ዑደት ጋር ለመራመድ እንዲቻል የተቋቋመ ኮርፖሬሽን ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ሌንሳ መኮንን በመግባቢያ ስምምነት ፊርማው ወቅት ሲናገሩ፤ እንደ አርክቴክቶች ማህበር ካሉ ማህበራት ጋር የትብብር ስራ መስራት ማህበራቱ ያላቸውን እምቅ አቅም በመጠቀም ኮርፖሬሽኑ የሚያከናውናቸውን የመሬት ይዞታ ልማት ጥረቶች በጋራ ለማስተሳሰር የሚያስችል አይነተኛ ስልት ነው ብለዋል፡፡ ዋና ስራ አስፋፃሚዋ አክለውም፤ ˝ለራዕያችን መሳካት ልምዶቻችንን በመጋራትና የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎቱን በአግባቡ እንጠቀማለን˝ ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በዚህ የትብብር ስምምነት መሰረት ሁለቱ አካላት በአዲስ አበባ የከተማ ልማት ስራዎች ያሉትን ተዛማጅ ፕላኖች፣ ዲዛይኖች እና ስትራቴጆዎችን በጋራ ለመገምገም፣ የፌዴራል መንግሥት ጽ/ቤቶች ልማትን የተመለከተ ዓለም አቀፍ ትንተናና የርዕሰ ብሔሩን መቀመጫ መቀየርን አካቶ የፌዴራል መንግሥት ጽ/ቤቶች በጋራ ዲዛይን ለማውጣት እንዲሁም በልዩ ሁኔታ በተመረጡ የክልል ከተማ አስተዳደሮች በመሬት ይዞታ ዙሪያ የጋራ ዲዛይን መስራት እና ተከታታይ የውይይት መድረኮችን ከማዘጋጀት በተጨማሪ የማህበሩን አቅም በማጠናከር ተከታታይነት ባለው ሁኔታ ትብብሩን በማጠናከር በጋራ ኃብት መፍጠር መቻልን ያካተተ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል ተሾመ በስምምነቱ አስፈላጊነት ዙሪያ ሲናገሩ፤ ማህበራቸው ለኮርፖሬሽኑ የተሰጠውን ኃላፊነት እንደሚያደንቅ የገለፁ ሲሆን ይህም ለከተሞች እና ፋሲሊቲዎች የተሳሰረ እና ሁለንተናዊ ዕድገት አይነተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ አቶ አማኑኤል አክለውም፤ የመግባቢያ ስምምነቱ የማህበሩ አባላት አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በማስቻል ለዜጎች ምቹ የሆኑ ማህበረ-ኢኮኖሚያቸው የጎላ ከተሞችን በመፍጠር እና ዳግም እንዲያንሰራሩ ለማድረግ እንደሚያስቸል ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ወ/ት ሌንሳ የኮሮናቫይረስ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት በመቀነስ ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን በማከናወን ስራ እንዳይስተጓጎል ማድረጉን ገልፀዋል፡፡ እንዲህ ባሉ ፈታኝ ወቅቶች አማራጭ መንገዶችን መፈለግ አለብን ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ የመፍትሔ አቅጣጫዎች በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘንድ ተግባራዊ መሆን አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top